የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 42

42
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ ፍረ​ድ​ልኝ፥
ከጽ​ድቅ ከወጡ ሕዝ​ብም በቀ​ሌን ተበ​ቀል።
ከዐ​መ​ፀ​ኛና ከሸ​ን​ጋይ ሰው አድ​ነኝ።
2አንተ አም​ላኬ፥ ኀይ​ሌም ነህና፥ ለምን ትተ​ወ​ኛ​ለህ?
ጠላ​ቶቼ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?
3ብር​ሃ​ን​ህ​ንና ጽድ​ቅ​ህን ላክ፤
እነ​ር​ሱም ይም​ሩኝ፥
አቤቱ ወደ መቅ​ደ​ስህ ተራ​ራና ወደ ማደ​ሪ​ያህ ይው​ሰ​ዱኝ።
4ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥
ጐል​ማ​ስ​ነ​ቴ​ንም ደስ ወዳ​ሰ​ኛት ወደ አም​ላኬ እገ​ባ​ለሁ፤
አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በመ​ሰ​ንቆ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።
5ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ?
የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ