መዝሙረ ዳዊት 43
43
ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች ትምህርት።
1አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥
አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
2እጅህ ጠላትን#ዕብ. “አሕዛብ” ይላል። አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤
አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም።
3በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥
ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤
ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤
ይቅር ብለሃቸዋልና።
4አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤
ለያዕቆብ መድኀኒትን ያዘዝህ።
5በአንተ ጠላቶቻችንን ሁሉ እንወጋቸዋለን፥
በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።
6በቀስቴ የምታመን አይደለሁም፥
ጦሬም አያድነኝም፤
7አንተ ግን ከከበቡን#ዕብ. “ከጠላቶቻችን” ይላል። አዳንኸን፥
የሚጠሉንንም ሁሉ አሳፈርሃቸው።
8ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥
ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
9አሁን ግን ጣልኸን፥ አሳፈርኸንም፥#በግእዝ ብቻ።
አምላካችን፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
10በጠላቶቻችን ዘንድ ወደ ኋላችን መለስኸን፥
ጠላቶቻችንም ተነጣጠቁን።
11እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥
ወደ አሕዛብም በተንኸን፥
12ሕዝብህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥
ለእልልታችንም ብዛት የለውም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመለወጣቸውም ትርፍ የለም” ይላል።
13ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥
በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።
14ለአሕዛብ ተረት፥
ለሕዝቡም የራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።
15እፍረቴ ሁልጊዜ በፊቴ ነው፥
እፍረት ፊቴን ሸፈነኝ።
16ከሚሳደብና ከሚላገድ ቃል የተነሣ፥
ከሚከብብ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚያሳድድ” ይላል። ጠላት ፊት የተነሣ ነው።
17ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥
አልረሳንህም፥ ኪዳንህንም አላፈረስንም።
18ልባችንም ወደ ኋላው አልተመለሰም፥
ፍለጋችንም ከመንገድህ ፈቀቅ አላለም፤
19 # ዕብ. “በአራዊት ስፍራ ሰብረኸናል” ይላል። በክፉ ስፍራ አዋርደኸናልና፥
የሞት ጥላም ሰውሮናልና፥
20የአምላካችንን ስም ረስተንስ ቢሆን፥
እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንሥተንስ ቢሆን፥
21እግዚአብሔር ይህን በተመራመረው ነበር!
እርሱ ልባችን የሰወረውን ያውቃልና።
22ስለ እርሱ#ዕብ. “ስለ አንተ” ይላል። ሁልጊዜ ይገድሉናልና፥
እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።
23አቤቱ፥ ንቃ፤ ለምንስ ትተኛለህ?
ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።
24ለምንስ ፊትህን ከእኛ ትመልሳለህ?
መከራችንንና ችግራችንንስ ለምን ትረሳለህ?
25ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቍላለችና፥
ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለችና።
26አቤቱ፥ ተነሥና ርዳን፥
ስለ ስምህም ተቤዥን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 43: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 43
43
ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች ትምህርት።
1አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥
አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
2እጅህ ጠላትን#ዕብ. “አሕዛብ” ይላል። አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤
አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም።
3በጦራቸው ምድርን አልወረሱም፥
ክንዳቸውም አላዳናቸውም፤
ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤
ይቅር ብለሃቸዋልና።
4አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤
ለያዕቆብ መድኀኒትን ያዘዝህ።
5በአንተ ጠላቶቻችንን ሁሉ እንወጋቸዋለን፥
በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።
6በቀስቴ የምታመን አይደለሁም፥
ጦሬም አያድነኝም፤
7አንተ ግን ከከበቡን#ዕብ. “ከጠላቶቻችን” ይላል። አዳንኸን፥
የሚጠሉንንም ሁሉ አሳፈርሃቸው።
8ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥
ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
9አሁን ግን ጣልኸን፥ አሳፈርኸንም፥#በግእዝ ብቻ።
አምላካችን፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
10በጠላቶቻችን ዘንድ ወደ ኋላችን መለስኸን፥
ጠላቶቻችንም ተነጣጠቁን።
11እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥
ወደ አሕዛብም በተንኸን፥
12ሕዝብህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥
ለእልልታችንም ብዛት የለውም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በመለወጣቸውም ትርፍ የለም” ይላል።
13ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥
በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።
14ለአሕዛብ ተረት፥
ለሕዝቡም የራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።
15እፍረቴ ሁልጊዜ በፊቴ ነው፥
እፍረት ፊቴን ሸፈነኝ።
16ከሚሳደብና ከሚላገድ ቃል የተነሣ፥
ከሚከብብ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚያሳድድ” ይላል። ጠላት ፊት የተነሣ ነው።
17ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥
አልረሳንህም፥ ኪዳንህንም አላፈረስንም።
18ልባችንም ወደ ኋላው አልተመለሰም፥
ፍለጋችንም ከመንገድህ ፈቀቅ አላለም፤
19 # ዕብ. “በአራዊት ስፍራ ሰብረኸናል” ይላል። በክፉ ስፍራ አዋርደኸናልና፥
የሞት ጥላም ሰውሮናልና፥
20የአምላካችንን ስም ረስተንስ ቢሆን፥
እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንሥተንስ ቢሆን፥
21እግዚአብሔር ይህን በተመራመረው ነበር!
እርሱ ልባችን የሰወረውን ያውቃልና።
22ስለ እርሱ#ዕብ. “ስለ አንተ” ይላል። ሁልጊዜ ይገድሉናልና፥
እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።
23አቤቱ፥ ንቃ፤ ለምንስ ትተኛለህ?
ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።
24ለምንስ ፊትህን ከእኛ ትመልሳለህ?
መከራችንንና ችግራችንንስ ለምን ትረሳለህ?
25ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጐሳቍላለችና፥
ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለችና።
26አቤቱ፥ ተነሥና ርዳን፥
ስለ ስምህም ተቤዥን።