መዝሙረ ዳዊት 44
44
ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የቆሬ ልጆች ትምህርት የፍቅር መዝሙር።
1ልቤ መልካም ነገርን ተናገረ፥
እኔም ሥራዬን ለንጉሥ እናገራለሁ፤
አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
2ውበቱ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ውበትህ” ይላል። ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል፤
ሞገስ ከከንፈሮችህ ፈሰሰ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ።
3ኀያል ሆይ፥ በደም ግባትህና በውበትህ፥
ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።
4ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም
አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤
ቀኝህም በክብር ይመራሃል።
5ኀያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥#ዕብ. “ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ናቸው” ይላል።
አሕዛብ በበታችህ ይወድቃሉ።
በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥
6አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፤
በትረ መንግሥትህ የጽድቅ በትር ነው።
7ጽድቅን ወደድህ፥ ዐመፃንም ጠላህ፤
ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ
እግዚአብሔር አምላክህ የደስታ ዘይትን ቀባህ።
8ከርቤና ሽቱ ዝባድም በልብሶችህ ናቸው።#ዕብ. “ደስ ያሰኙሃል” ይላል።
9የንግሥት#ዕብ. “የነገሥት” ይላል። ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤
በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
10ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤
ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤
11ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥
እርሱ ጌታሽ ነውና።
12የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል።
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ።
13ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤
በወርቀ ዘቦ ልብስ የተጐናጸፈችና የተሸፋፈነች ናት።
14በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሡ ይወስዳሉ፥
ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤
15በደስታና በሐሤት ይወስዱአቸዋል።
ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል።
16በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።
17ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ፤
አቤቱ፥ ስለዚህ ለዓለምና ለዘለዓለም።
አሕዛብ ያመሰግኑሃል።#መዝ. 44 ከቁ. 16 እስከ 17 በዕብ. 2ኛ መደብ ተባዕታይ ፆታ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 44: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 44
44
ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የቆሬ ልጆች ትምህርት የፍቅር መዝሙር።
1ልቤ መልካም ነገርን ተናገረ፥
እኔም ሥራዬን ለንጉሥ እናገራለሁ፤
አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።
2ውበቱ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ውበትህ” ይላል። ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል፤
ሞገስ ከከንፈሮችህ ፈሰሰ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ።
3ኀያል ሆይ፥ በደም ግባትህና በውበትህ፥
ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።
4ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም
አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤
ቀኝህም በክብር ይመራሃል።
5ኀያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥#ዕብ. “ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ናቸው” ይላል።
አሕዛብ በበታችህ ይወድቃሉ።
በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥
6አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፤
በትረ መንግሥትህ የጽድቅ በትር ነው።
7ጽድቅን ወደድህ፥ ዐመፃንም ጠላህ፤
ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ
እግዚአብሔር አምላክህ የደስታ ዘይትን ቀባህ።
8ከርቤና ሽቱ ዝባድም በልብሶችህ ናቸው።#ዕብ. “ደስ ያሰኙሃል” ይላል።
9የንግሥት#ዕብ. “የነገሥት” ይላል። ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤
በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
10ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ፥ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤
ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤
11ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥
እርሱ ጌታሽ ነውና።
12የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል።
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ።
13ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤
በወርቀ ዘቦ ልብስ የተጐናጸፈችና የተሸፋፈነች ናት።
14በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሡ ይወስዳሉ፥
ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤
15በደስታና በሐሤት ይወስዱአቸዋል።
ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል።
16በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።
17ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ፤
አቤቱ፥ ስለዚህ ለዓለምና ለዘለዓለም።
አሕዛብ ያመሰግኑሃል።#መዝ. 44 ከቁ. 16 እስከ 17 በዕብ. 2ኛ መደብ ተባዕታይ ፆታ ነው።