የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 46

46
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝ​ሙር።
1አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥
በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልዑል፥ ግሩ​ምም ነውና፥
በም​ድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
3አሕ​ዛ​ብን ከእኛ በታች፥
ወገ​ኖ​ች​ንም ከእ​ግ​ራ​ችን በታች አስ​ገ​ዛ​ልን።
4ለር​ስቱ እኛን መረ​ጠን፥
የያ​ዕ​ቆ​ብን ውበት የወ​ደደ።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ል​ልታ፥
ጌታ​ች​ንም በመ​ለ​ከት ድምፅ ዐረገ።
6ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ዘምሩ፤
ዘምሩ፥ ለን​ጉ​ሣ​ችን ዘምሩ።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤
በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ላይ ነገሠ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀ​መ​ጣል።
9የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤
የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ