የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 47

47
በሁ​ለ​ተኛ ሰን​በት ማግ​ሥት የቆሬ ልጆች የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፤
በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ በመ​ቅ​ደሱ ተራራ ምስ​ጋ​ናው ብዙ ነው።
2ለም​ድር ሁሉ ደስ​ታን የሚ​ያ​ዝዝ፥
የጽ​ዮን ተራ​ራ​ዎች በመ​ስዕ በኩል ናቸው።
የታ​ላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።
3በተ​ቀ​በ​ሏት ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ት​ዋን ያው​ቃል#መዝ. 47 ቍ. 3 ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላ​ላቅ ቤቶ​ችዋ የመ​ጠ​ጊያ አንባ ሆኖ ይታ​ወ​ቃል” ይላል።
4እነሆ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ተሰ​ብ​ስ​በው በአ​ን​ድ​ነት መጥ​ተ​ዋል።
5እነ​ር​ሱስ ይህን አይ​ተው አደ​ነቁ፥ ደነ​ገጡ፥ ፈሩም።
6መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም ያዛ​ቸው፥ እንደ ወላ​ድም በዚያ አማጡ።
7በኀ​ይ​ለኛ ነፋስ የተ​ር​ሴ​ስን መር​ከ​ቦች ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።
8እን​ደ​ሰ​ማን እን​ዲሁ አየን፥
በሠ​ራ​ዊት ጌታ ከተማ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ታል።
9አም​ላክ ሆይ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይቅ​ር​ታ​ህን ተቀ​በ​ልን።
10አም​ላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ
እን​ዲ​ሁም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስ​ጋ​ናህ ነው።
ቀኝህ ጽድ​ቅን የተ​መላ ነው።
11አቤቱ፥ ስለ ፍር​ድህ የጽ​ዮን ተራ​ሮች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥
የይ​ሁ​ዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት ያደ​ር​ጋሉ።
12ጽዮ​ንን ክበ​ቡ​አት፥ ዕቀ​ፉ​አ​ትም።
በቅ​ጥ​ሮ​ች​ዋም ተና​ገሩ፤
13በብ​ር​ታቷ ልባ​ች​ሁን አኑሩ፤
በረ​ከ​ቷ​ንም ትካ​ፈ​ላ​ላ​ችሁ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቍጠሩ” ይላል።
ለሚ​መ​ጣ​ውም ትው​ልድ ትነ​ግሩ ዘንድ።
14ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይህ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ሆነ፥
እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​ብ​ቀ​ናል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ