መዝሙረ ዳዊት 46
46
ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥
በደስታ ቃልም ለአግዚአብሔር እልል በሉ።
2እግዚአብሔር ልዑል፥ ግሩምም ነውና፥
በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
3አሕዛብን ከእኛ በታች፥
ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን።
4ለርስቱ እኛን መረጠን፥
የያዕቆብን ውበት የወደደ።
5እግዚአብሔር በእልልታ፥
ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤
ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
7እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤
በማስተዋል ዘምሩ፤
8እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፤
እግዚአብሔር በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
9የአሕዛብ አለቆች ከአብርሃም አምላክ ጋር ተሰበሰቡ፤
የምድር ኀይለኞች ለእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብለዋልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 46: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ