የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 50

50
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ወደ ቤር​ሳ​ቤህ ከገባ በኋላ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤
እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን#ዕብ. “መተ​ላ​ለ​ፌን” ይላል። ደም​ስስ።
2ከበ​ደሌ ፈጽሞ እጠ​በኝ፥
ከኀ​ጢ​አ​ቴም አን​ጻኝ፤
3እኔ በደ​ሌን አው​ቃ​ለ​ሁና፥
ኀጢ​አ​ቴም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።
4አን​ተን ብቻ በደ​ልሁ፥
በፊ​ት​ህም ክፋ​ትን አደ​ረ​ግሁ፥
በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ።#ዕብ. “ንጹሕ ትሆን ዘንድ” ይላል።
5እነሆ፥ በኀ​ጢ​አት ተፀ​ነ​ስሁ፥
እና​ቴም በዐ​መፃ ወለ​ደ​ችኝ።
6እነሆ፥ እው​ነ​ትን ወደ​ድህ፤
የማ​ይ​ነ​ገር ስውር ጥበ​ብ​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ኸኝ።
7በሂ​ሶጵ እር​ጨኝ፥ እነ​ጻ​ማ​ለሁ፤
እጠ​በኝ፥ ከበ​ረ​ዶም ይልቅ ነጭ እሆ​ና​ለሁ።
8ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታን አሰ​ማኝ፥
የጻ​ድ​ቃን አጥ​ን​ቶች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
9ከኀ​ጢ​አቴ ፊት​ህን መልስ፥
በደ​ሌ​ንም ሁሉ ደም​ስ​ስ​ልኝ።
10አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠ​ር​ልኝ፥
የቀ​ና​ው​ንም መን​ፈስ በው​ስጤ አድስ።
11ከፊ​ትህ አት​ጣ​ለኝ፥
ቅዱስ መን​ፈ​ስ​ህ​ንም ከእኔ ላይ አት​ው​ሰ​ድ​ብኝ።
12ደስ​ታ​ንና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የማ​ዳ​ን​ህን ደስታ” ይላል። ማዳ​ን​ህን ስጠኝ፥
በጽኑ መን​ፈ​ስም አጽ​ናኝ።
13መን​ገ​ድ​ህን ለኃ​ጥ​ኣን አስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ፥
ዝን​ጉ​ዎ​ችም ወደ አንተ ይመ​ለሱ ዘንድ።
14የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥
ከደም አድ​ነኝ፥ አን​ደ​በ​ቴም በአ​ንተ ጽድቅ ደስ ይለ​ዋል።
15አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥
አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።
16መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብት​ወ​ድ​ድስ በሰ​ጠ​ሁህ ነበር፤
የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አት​ወ​ድ​ድም።#ዕብ. “ደስ አያ​ሰ​ኝ​ህም” ይላል።
17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የዋህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የተ​ሰ​በረ” ይላል። መን​ፈስ ነው፥
የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንና የዋ​ሁን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ን​ቅም።
18አቤቱ፥ በው​ዴ​ታህ ጽዮ​ንን አሰ​ማ​ም​ራት፤
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጽ​ሮች ይታ​ነጹ።
19የጽ​ድ​ቁን መሥ​ዋ​ዕት፥
መባ​ው​ንም፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በወ​ደ​ድህ ጊዜ፥
ያን​ጊዜ በመ​ሠ​ዊ​ያህ ላይ ፍሪ​ዳ​ዎ​ችን ይሠ​ዋሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ