መዝሙረ ዳዊት 51
51
ለመዘምራን አለቃ ዶይቅ ኤዶማዊው መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቤሜሌክ ቤት መጥቶአል ብሎ በነገረው ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1 # ከግእዙ ይለያል። ኀያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኰራለህ?
ሁልጊዜስ ለምን ትበድላለህ?
2 # ዕብ. “አንደበትህ” ይላል። ልብህ ኀጢአትን ያስባል፤
እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።
3ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥
ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ።
4የሚያሰጥም የምላስ ነገርን ሁሉ#ከዕብራይስጥ ይለያል። ወደድህ።
5ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤
ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥
ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
6ጻድቃን አይተው ይፍሩ፤
በእርሱም ይሳቁ እንዲህም ይበሉ፦
7“እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥
በባለጠግነቱም ብዛት የታመነ፥
በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።”
8እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤
ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንሁ።
9አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥
በጻድቃንህም#ዕብ. “ቅዱሳንህ” ይላል። ዘንድ መልካም ነውና ምሕረትህን#ዕብ. “ስምህን አከብራለሁ”ይላል። ተስፋ አደርጋለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 51: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ