የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 51

51
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ዶይቅ ኤዶ​ማ​ዊው መጥቶ ለሳ​ኦል፦ ዳዊት ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ቤት መጥ​ቶ​አል ብሎ በነ​ገ​ረው ጊዜ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1 # ከግ​እዙ ይለ​ያል። ኀያል ሆይ፥ በክ​ፋት ለምን ትኰ​ራ​ለህ?
ሁል​ጊ​ዜስ ለምን ትበ​ድ​ላ​ለህ?
2 # ዕብ. “አን​ደ​በ​ትህ” ይላል። ልብህ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ባል፤
እንደ ተሳለ ምላጭ ሽን​ገ​ላን አደ​ረ​ግህ።
3ከመ​ል​ካም ይልቅ ክፋ​ትን፥
ጽድ​ቅ​ንም ከመ​ና​ገር ይልቅ ዐመ​ፃን ወደ​ድህ።
4የሚ​ያ​ሰ​ጥም የም​ላስ ነገ​ርን ሁሉ#ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ይለ​ያል። ወደ​ድህ።
5ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያፈ​ር​ስ​ሃል፤
ከቤ​ት​ህም ይነ​ቅ​ል​ሃል፥ ያፈ​ል​ስ​ሃ​ልም፥
ሥር​ህ​ንም ከሕ​ያ​ዋን ምድር።
6ጻድ​ቃን አይ​ተው ይፍሩ፤
በእ​ር​ሱም ይሳቁ እን​ዲ​ህም ይበሉ፦
7“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥
በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥
በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”
8እኔስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ለመ​ለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤
ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ታመ​ንሁ።
9አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥
በጻ​ድ​ቃ​ን​ህም#ዕብ. “ቅዱ​ሳ​ንህ” ይላል። ዘንድ መል​ካም ነውና ምሕ​ረ​ት​ህን#ዕብ. “ስም​ህን አከ​ብ​ራ​ለሁ”ይላል። ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ