የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 52

52
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በማ​ኸ​ላት የዳ​ዊት መዝ​ሙር ፍጻሜ።
1ሰነፍ በልቡ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም ይላል።
ረከሱ፥ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጐሰ​ቈሉ፤
በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ አስ​ተ​ዋይ እን​ዳለ ያይ ዘንድ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።
3ሁሉ ተካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት በደለ፤#ዕብ. “ሁሉ በደሉ አብ​ረ​ውም ረከሱ” ይላል።
አንድ ስንኳ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።
4ሕዝ​ቤን እን​ጀ​ራን እንደ መብ​ላት የሚ​በሉ
ግፍ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሁሉ አያ​ው​ቁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አይ​ጠ​ሩ​ትም።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና
በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።
6መድ​ኀ​ኒ​ትን ከጽ​ዮን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል?
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥
ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ