መዝሙረ ዳዊት 52
52
ለመዘምራን አለቃ በማኸላት የዳዊት መዝሙር ፍጻሜ።
1ሰነፍ በልቡ፦ እግዚአብሔር የለም ይላል።
ረከሱ፥ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤
በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።
2እግዚአብሔርን የሚፈልግ አስተዋይ እንዳለ ያይ ዘንድ
እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
3ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ፤#ዕብ. “ሁሉ በደሉ አብረውም ረከሱ” ይላል።
አንድ ስንኳ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።
4ሕዝቤን እንጀራን እንደ መብላት የሚበሉ
ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁም እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
5እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና
በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤
እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ።
6መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን ይሰጣል?
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 52: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 52
52
ለመዘምራን አለቃ በማኸላት የዳዊት መዝሙር ፍጻሜ።
1ሰነፍ በልቡ፦ እግዚአብሔር የለም ይላል።
ረከሱ፥ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤
በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።
2እግዚአብሔርን የሚፈልግ አስተዋይ እንዳለ ያይ ዘንድ
እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
3ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ፤#ዕብ. “ሁሉ በደሉ አብረውም ረከሱ” ይላል።
አንድ ስንኳ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።
4ሕዝቤን እንጀራን እንደ መብላት የሚበሉ
ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁም እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
5እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና
በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤
እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ።
6መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን ይሰጣል?
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል።