መዝሙረ ዳዊት 53
53
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥
በኀይልህም ፍረድልኝ።
2አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥
የአፌንም ቃል አድምጥ፤
3ባዕዳን በእኔ ላይ ቆመዋልና፥
ኀያላንም ነፍሴን ሽተዋታልና።
እግዚአብሔርንም በፊታቸው አላደረጉትም።
4እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥
ጌታዬም ነፍሴን ያድናታል።#ዕብ. “ደጋፊዋ ነው” ይላል።
5ክፋትን ወደ ጠላቶች ይመልሳታል፤
በእውነትህም አጥፋቸው።
6ከፈቃዴ የተነሣ እሠዋልሃለሁ፤
አቤቱ፥ መልካም ነውና፥ ስምህን አመሰግናለሁ፤
7ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና፥
ዐይኔም በጠላቶቼ ላይ አይታለችና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 53: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 53
53
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥
በኀይልህም ፍረድልኝ።
2አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥
የአፌንም ቃል አድምጥ፤
3ባዕዳን በእኔ ላይ ቆመዋልና፥
ኀያላንም ነፍሴን ሽተዋታልና።
እግዚአብሔርንም በፊታቸው አላደረጉትም።
4እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥
ጌታዬም ነፍሴን ያድናታል።#ዕብ. “ደጋፊዋ ነው” ይላል።
5ክፋትን ወደ ጠላቶች ይመልሳታል፤
በእውነትህም አጥፋቸው።
6ከፈቃዴ የተነሣ እሠዋልሃለሁ፤
አቤቱ፥ መልካም ነውና፥ ስምህን አመሰግናለሁ፤
7ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና፥
ዐይኔም በጠላቶቼ ላይ አይታለችና።