መዝሙረ ዳዊት 66
66
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥
ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ እኛም በሕይወት እንኑር
2መንገድህን በምድር፥
በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ ማዳንህን እናውቅ ዘንድ፥
3አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል፥
አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል።
አሕዛብ ደስ ይላቸዋል፥ ሐሤትም ያደርጋሉ።
4ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥
አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና
5አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል።
አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል።
6ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።
7እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ ይፈሩታል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 66: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 66
66
ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥
ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ እኛም በሕይወት እንኑር
2መንገድህን በምድር፥
በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ ማዳንህን እናውቅ ዘንድ፥
3አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል፥
አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል።
አሕዛብ ደስ ይላቸዋል፥ ሐሤትም ያደርጋሉ።
4ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥
አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና
5አቤቱ፥ አሕዛብ ያመሰግኑሃል።
አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑሃል።
6ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።
7እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ ይፈሩታል።