መዝሙረ ዳዊት 72
72
የአሳፍ መዝሙር።
1ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እጅግ ቸር ነው።
2እኔ ግን እግሮች ሊሰናከሉ፥
አረማመዴም ሊወድቅ ጥቂት ቀረ።
3የዐመፀኞችን ሰላም አይቼ
በኃጥኣን ላይ ቀንቼ ነበርና።
4ለሞታቸው እረፍት#ዕብ. “መጣጣር” ይላል። የለውምና፤
ለመቅሠፍታቸውም#ዕብ. “ኀይላቸው ጠንካራ ነውና” ይላል። ኀይል የለውምና፤
5በድካምም ጠላት አልሆኑም።
ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6ስለዚህም ትዕቢት ያዛቸው፤
ኀጢአታቸውንና በደላቸውን ተጐናጸፉአት።
7 # ከዕብራይስጥ ይለያል። መቅን ከቅልጥም እንደሚወጣ ኀጢአታቸው ይወጣል።
ልባቸውም ከትዕቢት አለፈ።
8ዐስበው ከንቱ ነገርን ተናገሩ።
በአርያምም ዐመፃን ተናገሩ።
9አፋቸውንም በሰማይ አኖሩ፥
አንደበታቸውም በምድር ላይ ተመላለሰ።
10ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤
ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤
11“እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?
በአርያምስ በውኑ የሚያውቅ አለን?”#ዕብ. “በልዑልስ ዘንድ በውኑ ዕውቀት አለን” ይላል። ይላሉ።
12እነሆ፥ እነዚህ ኃጥኣን ደስ ይላቸዋል፤
ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያጸኗታል፤
13እንዲህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁአትን?”
እጆቼንም በንጽሕና አጠብሁ።
14ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥
መሰደቤም በማለዳ ነው።
15እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥
እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16አውቅም ዘንድ ተቀበልኸኝ፥#ዕብ. “ዐሰብሁ” ይላል።
ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።
17ፍጻሜአቸውን አውቅ ዘንድ
ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
18ነገር ግን ስለ ሽንገላቸው አቈየሃቸው፥
በመነሣታቸውም ጣልኻቸው።
19እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥
ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ።
20ከእንቅልፍ እንደሚነቃ፥
አቤቱ፥ በከተማህ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።
21ልቤ ነድዶአል፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤
22እኔ የተናቅሁ ነኝ፥ አላወቅሁምም፥
በአንተ ዘንድ እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥
ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24በአንተ ምክር መራኸኝ፤
በክብርም ተቀበልኸኝ።
25 # ግእዙ “ምንት ብከ ተሀሉ ውስተ ሰማይ?” ይላል። በሰማይ ያለኝ ምንድን ነው?
በምድርስ ውስጥ ከአንተ በቀር ምን እሻለሁ?
26የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤
እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ዕድል ፋንታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤
ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።
28ለእኔ ግን እግዚአብሔርን መከተል ይሻለኛል፤
መታመኛዬም በእግዚአብሔር ላይ ነው
በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 72: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 72
72
የአሳፍ መዝሙር።
1ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እጅግ ቸር ነው።
2እኔ ግን እግሮች ሊሰናከሉ፥
አረማመዴም ሊወድቅ ጥቂት ቀረ።
3የዐመፀኞችን ሰላም አይቼ
በኃጥኣን ላይ ቀንቼ ነበርና።
4ለሞታቸው እረፍት#ዕብ. “መጣጣር” ይላል። የለውምና፤
ለመቅሠፍታቸውም#ዕብ. “ኀይላቸው ጠንካራ ነውና” ይላል። ኀይል የለውምና፤
5በድካምም ጠላት አልሆኑም።
ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6ስለዚህም ትዕቢት ያዛቸው፤
ኀጢአታቸውንና በደላቸውን ተጐናጸፉአት።
7 # ከዕብራይስጥ ይለያል። መቅን ከቅልጥም እንደሚወጣ ኀጢአታቸው ይወጣል።
ልባቸውም ከትዕቢት አለፈ።
8ዐስበው ከንቱ ነገርን ተናገሩ።
በአርያምም ዐመፃን ተናገሩ።
9አፋቸውንም በሰማይ አኖሩ፥
አንደበታቸውም በምድር ላይ ተመላለሰ።
10ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤
ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤
11“እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?
በአርያምስ በውኑ የሚያውቅ አለን?”#ዕብ. “በልዑልስ ዘንድ በውኑ ዕውቀት አለን” ይላል። ይላሉ።
12እነሆ፥ እነዚህ ኃጥኣን ደስ ይላቸዋል፤
ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያጸኗታል፤
13እንዲህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁአትን?”
እጆቼንም በንጽሕና አጠብሁ።
14ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥
መሰደቤም በማለዳ ነው።
15እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥
እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16አውቅም ዘንድ ተቀበልኸኝ፥#ዕብ. “ዐሰብሁ” ይላል።
ይህ ግን በፊቴ ድካም ነው።
17ፍጻሜአቸውን አውቅ ዘንድ
ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
18ነገር ግን ስለ ሽንገላቸው አቈየሃቸው፥
በመነሣታቸውም ጣልኻቸው።
19እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥
ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ።
20ከእንቅልፍ እንደሚነቃ፥
አቤቱ፥ በከተማህ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።
21ልቤ ነድዶአል፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤
22እኔ የተናቅሁ ነኝ፥ አላወቅሁምም፥
በአንተ ዘንድ እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥
ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24በአንተ ምክር መራኸኝ፤
በክብርም ተቀበልኸኝ።
25 # ግእዙ “ምንት ብከ ተሀሉ ውስተ ሰማይ?” ይላል። በሰማይ ያለኝ ምንድን ነው?
በምድርስ ውስጥ ከአንተ በቀር ምን እሻለሁ?
26የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤
እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ዕድል ፋንታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤
ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።
28ለእኔ ግን እግዚአብሔርን መከተል ይሻለኛል፤
መታመኛዬም በእግዚአብሔር ላይ ነው
በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።