መዝሙረ ዳዊት 74
74
ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
1አቤቱ አመሰግንሃለሁ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እናመሰግንሃለን” ይላል።
አመሰግንሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ፤
ተአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።
2ጊዜውን ባገኘሁ ጊዜ እኔ በቅን እፈርዳለሁ።
3ምድርና በእርስዋ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ቀለጡ፥
እኔም ምሰሶዎችዋን አጸናሁ።
4ኃጥኣንን አልኋቸው፥ “አትበድሉ”
የሚበድሉትንም አልኋቸው፥ “ቀንዳችሁን አታንሡ፥
5ቀንዳችሁን እስከ አርያም አታንሡ፥
በእግዚአብሔር ላይ ዐመፃን አትናገሩ።”
6ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤
7እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና
ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል።
8ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና፤
ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፤
ከዚህ ወደዚህ አቃዳው፥
ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፤
የምድር ኃጥኣን ሁሉ ይጠጡታል።
9እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥
ለያዕቆብም አምላክ እዘምራለሁ፥
10የኃጥኣንን ቀንዶች#ግእዝ “ራሶች” ይላል። ሁሉ እሰብራለሁ።
የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 74: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ