መዝ​ሙረ ዳዊት 95

95
ከም​ርኮ በኋላ ቤት በተ​ሠራ ጊዜ።
1ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፤
ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም ባርኩ፥
ዕለት ዕለ​ትም ማዳ​ኑን አውሩ።
3ክብ​ሩን ለአ​ሕ​ዛብ፥
ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም ለወ​ገ​ኖች ሁሉ ንገሩ፤
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ፥ ምስ​ጋ​ና​ውም ብዙ ነውና፥
በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ የተ​ፈራ ነውና።
5የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሁሉ አጋ​ን​ንት ናቸ​ውና፤
እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ግን ሰማ​ያ​ትን ፈጠረ።
6እም​ነ​ትና በጎ​ነት በፊቱ፥
ቅድ​ስ​ናና የክ​ብር ገና​ና​ነት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።
7የአ​ሕ​ዛብ ወገ​ኖች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥
ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፤
8ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስሙ ክብ​ርን አምጡ፤
መሥ​ዋ​ዕት ያዙ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ግቡ።
9ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ድ​ስ​ናው ቦታ ስገዱ፤
ምድር በመ​ላዋ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ ትነ​ዋ​ወ​ጣ​ለች።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንደ ነገሠ ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው፥
እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም ዓለ​ሙን ሁሉ አጸ​ናው፥
አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይገ​ዛል።
11ሰማ​ያት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለች፤
ባሕር ሞላዋ ትና​ወ​ጣ​ለች፤
12በረሃ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ ሁሉ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤
የዱር ዛፎች ሁሉ በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤
13ይመ​ጣ​ልና፤ በም​ድር ላይ ሊፈ​ርድ ይመ​ጣ​ልና፤
እር​ሱም ዓለ​ምን በጽ​ድቅ አሕ​ዛ​ብ​ንም በቅ​ን​ነት ይገ​ዛል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ