የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 5

5
በእ​ም​ነት ስለ መጽ​ደቅ
1እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ከጸ​ደ​ቅን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምን እና​ገ​ና​ለን። 2በእ​ር​ሱም አማ​ካ​ኝ​ነት ወደ​ቆ​ም​ን​በት ወደ ጸጋው በእ​ም​ነት ተመ​ራን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተስፋ እን​መ​ካ​ለን። 3የም​ን​መካ በእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ከ​ራ​ችን ደግሞ እን​መ​ካ​ለን እንጂ፤ መከራ በእና ላይ ትዕ​ግ​ሥ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​መጣ እና​ው​ቃ​ለ​ንና። 4ትዕ​ግ​ሥ​ትም መከራ ነው፤ በመ​ከ​ራም ተስፋ ይገ​ናል። 5ተስ​ፋም አያ​ሳ​ፍ​ርም፤ በሰ​ጠን በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በል​ባ​ችን መል​ቶ​አ​ልና። 6ክር​ስ​ቶ​ስም እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይሞት ዘንድ ዘመኑ ሲደ​ርስ መጣ።#ግሪኩ “ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ሞተ” ይላል። 7ስለ ክፉ​ዎች በጭ​ንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚ​ደ​ፍር አይ​ገ​ኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚ​ጨ​ክን የሚ​ገኝ እን​ዳለ እንጃ። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ያህል እንደ ወደ​ደን እነሆ፥ እዩ፤ እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ክር​ስ​ቶስ ስለ እና ሞተ። 9እን​ግ​ዲህ በደሙ ዛሬ ከጸ​ደ​ቅን ከሚ​መ​ጣው መከራ በእ​ርሱ እን​ድ​ና​ለን። 10እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቹ ስን​ሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታ​ረ​ቀን በኋ​ላም በልጁ ሕይ​ወት እን​ዴት የበ​ለጠ ያድ​ነን! 11በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ።
ሞት በአ​ዳም፥ ሕይ​ወ​ትም በክ​ር​ስ​ቶስ
12 # ዘፍ. 3፥6። ስለ​ዚ​ህም በአ​ንድ ሰው በደል ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለ​ዚ​ችም ኀጢ​አት ሞት ገባ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ ኀጢ​አ​ትን ስለ አደ​ረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ። 13ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢ​አት ምን እንደ ሆነች ሳት​ታ​ወቅ በዓ​ለም ውስጥ ነበ​ረች፤ ነገር ግን የኦ​ሪት ሕግ ገና ስላ​ል​መጣ ኀጢ​አት ተብላ አት​ቈ​ጠ​ርም ነበር። 14ነገር ግን በአ​ዳም ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ከአ​ዳም እስከ ሙሴ የበ​ደ​ሉ​ት​ንም ያል​በ​ደ​ሉ​ት​ንም ሞት ገዛ​ቸው፤ ሁሉ በአ​ዳም አም​ሳል ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፥ አዳ​ምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእ​ርሱ አም​ሳሉ ነውና።
15ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በበ​ደ​ላ​ችን መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ በአ​ንድ ሰው በደል ብዙ​ዎች ከሞቱ፥ እን​ግ​ዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ፥ በአ​ንዱ ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቤዛ​ነት በሰ​ጠን ሀብቱ ሕይ​ወት በብ​ዙ​ዎች ላይ እን​ዴት እጅግ ይበዛ ይሆን? 16የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ የኀ​ጢ​አት ፍርድ ከአ​ንድ ሰው ወጥታ ሁሉ ከተ​ቀ​ጣ​ባት፥ ጸጋው ከበ​ደ​ላ​ችን እንደ ምን ያነ​ጻን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንስ ሕይ​ወት እን​ዴት ይሰ​ጠን ይሆን?#የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንስ ሕይ​ወት እን​ዴት ይሰ​ጠን ይሆን?” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 17የአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት ሞትን ካነ​ገ​ሠ​ችው በአ​ንድ ሰው በደ​ልም ሞት ከገ​ዛን፥#“በአ​ንድ ሰው በደል ሞት ከገ​ዛን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። የአ​ንዱ ሰው የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጸ​ጋው ብዛ​ትና የጽ​ድቁ ስጦታ እን​ዴት እጅግ ያጸ​ድ​ቀን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ት​ንስ እን​ዴት ያበ​ዛ​ልን ይሆን?#“የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ት​ንስ እን​ዴት ያበ​ዛ​ልን ይሆን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም።
18እን​ግ​ዲህ በአ​ንዱ ሰው በደል ዓለም ሁሉ እንደ ተፈ​ረ​ደ​በት፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንዱ ሰው ጽድቅ ሰው ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል። 19በአ​ንድ ሰው አለ​መ​ታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ኀጢ​አ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ፥ እን​ዲሁ ደግሞ በአ​ንድ ሰው መታ​ዘዝ ብዙ​ዎች ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ። 20ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢ​አ​ትም ከበ​ዛች ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዛች። 21ኀጢ​አ​ትም ሞትን እንደ አነ​ገ​ሠ​ችው እን​ዲሁ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ጽድ​ቅን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ታነ​ግ​ሠ​ዋ​ለች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ