ወደ ሮሜ ሰዎች 6
6
ከኀጢአት ተለይቶ በክርስቶስ መኖር
1እንግዲህ ምን እንላለን? የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲበዛ ኀጢአት እንሥራን? አይደለም። 2ከኀጢአታችን የተለየን እኛ እንግዲህ እንዴት ዳግመኛ በእርስዋ ጸንተን መኖር እንችላለን? 3ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቅን እኛ ሁላችን በሞቱ እንደ ተጠመቅን ሁላችሁ ይህን ዕወቁ። 4#ቈላ. 2፥12። በሞቱም እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን፤ እርሱ ክርስቶስ በአባቱ ጌትነት ከሙታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐዲስ ሕይወት እንኖራለን።
5በሞቱ ከመሰልነውም በትንሣኤው እንመስለዋለን። 6ነገር ግን የኀጢአትን ሥጋ ይሽር ዘንድ ከእርሱ ጋር የተሰቀለው አሮጌው ሰውነታችን እንደ ሆነ ይህን እናውቃለን፤ ከእንግዲህ ወዲያ ዳግመና ለኀጢአት እንገዛ ዘንድ አንመለስም። 7የሞተስ ከኀጢአት ነጻ ወጥቶአል። 8ከክርስቶስ ጋር ከሞትንም ከእርሱ ጋር በሕይወት እንደምንኖር እናምናለን። 9ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ፥ ዳግመኛም እንደማይሞት፥ እንግዲህ ወዲህም ሞት እንደማይገዛው እናውቃለን። 10የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞቱም ኀጢአትን ሻራት፤ የተነሣም ለእግዚአብሔር ተነሣ። 11እንዲሁ እናንተም ራሳችሁን ለኀጢአት ምውታን አድርጉ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም ለእግዚአብሔር ሕያዋን ሁኑ።
12በዚህ በሚሞት ሰውነታችሁ ኀጢአትን አታንግሡአት፤ ለምኞቱም እሽ አትበሉት። 13ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጉ እንጂ ሰውነታችሁን ለኀጢአት የዐመፅ የጦር መሣሪያ አታድርጉት፤ ሰውነታችሁንም ለእግዚአብሔር የጽድቅ የጦር መሣሪያ አድርጉ። 14እንግዲህ ኀጢአት አትገዛችሁም፤ የኦሪትን ሕግ ከመሥራት ወጥታችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸጋ ገብታችኋልና።
ስለ መታዘዝ ምሥጢር
15እንግዲህ ምን እንላለን? የኦሪትን ሕግ ከመሥራት ወጥተን ወደ እግዚአብሔር ጸጋ ስለ ገባን ኀጢአት እንሥራን? አይደለም። 16ለምትታዘዙለት፥ እሺ ለምትሉትም እናንተ አገልጋዮች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ለተባበራችሁለትስ ራሳችሁን እንደ አስገዛችሁ አታውቁምን? ኀጢአትንም እሺ ብትሉአት፥ ተባብራችሁም ብትበድሉ እናንት ለሞት ተገዢዎች ትሆናላችሁ፤ ጽድቅንም እሺ ብትሉአት ለበጎ ሥራም ብትተባበሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁ። 17የኀጢአት ተገዦች ስትሆኑ ምሳሌነቱ ለተሰጣችሁ ለምትማሩት ትምህርት ታዝዛችኋልና እግዚአብሔር ይመስገን። 18አሁን ግን ከኀጢአት ነጻ ሁናችሁ ለጽድቅ ተገዝታችኋል። 19ስለ ሰውነታችሁ ድካም በሰው ልማድ እነግራችኋለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰውነታችሁን ለኀጢአትና ለርኵሰት፥ ለዐመፃም እንደ አስገዛችሁ፥ እንዲሁ አሁንም ሰውነታችሁን ለጽድቅና ለቅድስና አስገዙ። 20ለኀጢአት ትገዙ በነበረበት ጊዜ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁና። 21በዚያን ጊዜ ሥራችሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍሩበታላችሁ፤ መጨረሻው ሞት ነውና። 22ዛሬ ግን ከኀጢአት ነጻ ወጣችሁ፤ ራሳችሁንም ለጽድቅ አስገዛችሁ፤#በግሪኩ “ለእግዚአብሔር ተገዛችሁ” ይላል። ለቅድስናም ፍሬን አፈራችሁ፤ ፍጻሜው ግን የዘለዓለም ሕይወት ነው። 23የኀጢአት ትርፍዋ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ጸጋ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘለዓለም ሕይወት ነው።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 6: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ