ወደ ሮሜ ሰዎች 7
7
1ወንድሞቻችን! ሕግን ለሚያስተውሉ እናገራለሁና፤ ሰው በሕይወት ባለበት ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? 2ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚስትነት ታስራበት ከኖረችው ሕግ የተፈታች ናት። 3ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትሆናለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥታለች፤ ለሌላ ወንድ ብትሆንም አመንዝራ አትባልም።
4ወንድሞች ሆይ! እናንተ እንዲሁ የክርስቶስ አካል ስለ ሆናችሁ ከኦሪት ተለይታችኋል፤ ለእግዚአብሔርም ፍሬ እንድታፈሩ ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው ለዳግማዊ አዳም ሆናችኋል። 5የሰውን ሕግ በሠራን ጊዜ ግን በኦሪት ሕግ ደካማነት ቅጣቱ ጸናብን፤ ሞትንም አፈራን።#ምዕ. 7 ቍ. 5 ከግሪኩ ይለያል። 6አሁን ግን ታስረንበት ከነበረው ከኦሪት ሕግ ነፃ ወጥተናል፤ ስለዚህ በብሉይ መጽሐፍ ሳይሆን በአዲሱ መንፈሳዊ ሕይወት እንገዛለን።
ኦሪትን ስለ መተው
7 #
ዘፀ. 20፥17፤ ዘዳ. 5፥21። እንግዲህ ምን እንላለን? ኦሪት ኀጢአት ናትን? አይደለችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባትሠራ ኀጢአትን ባላወቅኋትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አትመኝ” ባትል ኖሮም ምኞትን ፈጽሞ ባላወቅኋትም ነበር። 8ያችም ትእዛዝ ለኀጢአት ምክንያት ሆነቻት፤ ምኞትንም ሁሉ አመጣችብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳትሠራ ኀጢአት ሙት ነበረች። 9እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳትሠራ ሕያው ነበርሁ፤ የኦሪት ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኀጢአት ሕይወትን አገኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ። 10ለሕይወት የተሠራችልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገኘኋት። 11#ዘፍ. 3፥13። ኀጢአት በዚያች ትእዛዝ ምክንያት አሳተችኝ፤ በእርሷም ገደለችኝ። 12አሁንም ቢሆን ኦሪትስ ቅድስት ናት፤ ትእዛዝዋም ቅዱስና እውነት ነው፤ መልካምም ነው፤ በረከትም ነው።#“በረከትም ነው” የሚለው በግሪኩ የለም።
13እንግዲህ ያ መልካም ነው ብዬ የማስበው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላለሁን? አይደለም፤ ነገር ግን ኀጢአት ኀጢአት እንደ ሆነች በታወቀች ጊዜ ሞትን አበዛችብኝ፤ ከዚያም ትእዛዝ የተነሣ ኀጢአተናው እንዲታወቅ፥ ኀጢአትም ተለይታ እንድትታወቅ ኦሪት መልካሙን ከክፉ ልትለይ ተሠርታለች።#“ኦሪትም መልካሙን ከክፉ ልትለይ ተሠርታለች” የሚለው በግሪኩ የለም።
ስለ መንፈሳዊ ሕግ
14የኦሪት ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለን፤ እኔ ግን ለኀጢአት የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ። 15#ገላ. 5፥17። የማደርገውን አላውቅምና፤ የምወደውንም ያን ምንም አላደርገውምና፤ ያንኑ የምጠላውን ብቻ እሠራለሁ እንጂ። 16የማልወደውን የምሠራ ከሆንሁ ግን ያ የኦሪት ሕግ መሠራት ለበጎ እንደ ሆነ ምስክሩ እኔ ነኝ። 17እንግዲያስ በእኔ ላይ ያደረች ኀጢአት ናት እንጂ፥ ያን የማደርገው እኔ አይደለሁም። 18በእኔ ማለት በሥጋዬ መልካም ነገር እንደማይኖር አውቃለሁ፤ መልካም ሥራ ለመሥራት መሻቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግባር መሥራት ግን የለኝም። 19ያን የምወደውንም በጎ ነገር የማደርግ አይደለም፤ ነገር ግን ያን የምጠላውን ክፉውን አደርጋለሁ። 20የማልወደውንስ የምሠራ ከሆነ የምሠራው እኔ አይደለሁም፤ በእኔ ላይ ያደረች ኀጢአት ናት እንጂ። 21መልካም ሥራ እንድሠራ የፈቀደልኝን ያን ሕግ እርሱ ክፉ ነገር አምጥቶብኝ አገኘሁት። 22በልቡናዬ ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር ሕግ መልካም ነው። 23ነገር ግን በሰውነቴ ውስጥ ያለውን ሌላ የኀጢአት ሕግ እመለከታለሁ፤ በልቡናዬም ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ተሰልፈው ተዋጉ፤ በሰውነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀጢአት ሕግም በረታና ወደ እርሱ ማረከኝ። 24እኔ ምንና ወራዳ ሰው ነኝ፤ ከዚህ ሟች ሰውነቴ ማን ባዳነኝ? 25በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እኔ በልቤ ለእግዚአብሔር ሕግ እገዛለሁ፤ በሥጋዬ ግን ለኀጢአት ሕግ እገዛለሁ።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 7: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ