መጽሐፈ ሲራክ 50
50
የኦንያ ልጅ ስምዖን
1የኦንያ ልጅ ታላቁ ካህን ስምዖንም
በሕይወቱ ቤተ መቅደስን አደሰ፤ በዘመኑም ቤተ መቅደስን አጸና።
2እንዲሁም የቅጥሩን መሠረት ዕጥፍ አድርጎ ሠራ
ካህን የሚለብሰውንም ቀጭን ልብስ ሠራ።
3በዘመኑም የውኃዎች ምንጮች አልጐደሉም፤
የጕድጓዱም ውኃ ብዛቱ እንደ ባሕር ውኃ ነበር።
4ሕዝቡም እንዳይወድቁ ይጠነቀቅላቸው ነበር፤
ከተማዋንም ከጠላት ለመከላከል መሸገ።
5ከቤተ መቅደስ መጋረጃ በወጣ ጊዜም በሕዝቡ መካከል ተከበረ።
6በደመና ውስጥ እንደ አጥቢያ ኮከብና
በምልዐት ቀን እንደ ሙሉ ጨረቃ ነበረ።
7በልዑል መቅደስም ላይ እንደምታበራ ፀሐይ ነበረ።
በብሩህ ደመናም ውስጥ ብርሃን እንደሚሰጥ ቀስተ ደመና ነበር።
8እንደ መጸው ወራት ጽጌረዳም ነበር፤
በውኃ መፍሰሻ አጠገብ እንደሚያፈራ አበባም ነበር፤
በመከርም ወራት እንደ ሊባኖስ ዛፍ ቅርንጫፍ ነበር።
9በጥና እሳት ላይ እንዳለ ነጭ ዕጣንም ነበር።
ተመትቶ እንደ ተሠራ የወርቅ ዕቃም ነበር።
በጌጥ ላይ እንዳለ የከበረ ዕንቍም ነበር፤
10ፍሬዋ ብዙ እንደ ሆነ የዘይት እንጨት፥
ከደመና በታች እንደሚያድግ የዋንዛ ዛፍ ነበር።
11እርሱም የክብር ልብሱን በለበሰ ጊዜ፥
የመመኪያውንም ጌጥ በለበሰ ጊዜ፥
ወደ ተቀደሰውም መሠዊያ በወጣ ጊዜ፥
በቅድስና ልብሱ ተከበረ።
12ከካህናቱም እጅ የመሥዋዕቱን ሥጋ ክፍል በተቀበለ ጊዜ፥
በመሠዊያው አጠገብ ይቆም ነበር፤
ወንድሞቹም በዙሪያው ቁመው ይጋርዱት ነበር፤
እንደ ሊባኖስ ለጋ ዝግባና እንደ ዘንባባም ዛፍ ይከቡት ነበር።
13እንዲሁም የአሮን ልጆች ሁሉ የክብር ልብሳቸውን ለብሰው፥
የእግዚአብሔርን መባእ በእጃቸው ይዘው፥
በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ፊት ይቆሙ ነበር።
14በመሠዊያውም ሥራቸውን ይፈጽሙ ነበር፤
ሁሉን የሚችል የልዑልንም መሥዋዕት ያዘጋጁ ነበር።
15የወይኑን ጽዋዕ ይዞ እጁን አነሣ፤
የወይኑን ዘለላ ደምም አፈሰሰ፤
ለንጉሠ ነገሥት ለልዑል በጎ መዓዛ አድርጎ
በመሠዊያው እግር ሥር ያፈስሰው ነበር።
16የአሮንም ልጆች እየጮሁ ምስጋናውን ይናገሩ ነበር፤
ተመትቶ የተሠራ የብር መለከትንም ይነፉ ነበር፤
በልዑልም ፊት ማሰባሰቢያ ሊሆን ቃላቸውን ያሰሙ ነበር።
17ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ያርፉ ነበር፤
በምድር ላይም በግንባራቸው ይሰግዱ ነበር፤
ሁሉን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርቡ ነበር።
18መዘምራኑም በቃላቸው ያመሰግኑት ነበር፥
የዜማቸውም ድምፅ ቤቱን ያስተጋባው ነበር።
19ሕዝቡም ወደ ልዑል እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር፤
በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ሥርዐቱን እስኪጨርሱ ድረስ
ይቅር በሚል በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ነበር፤ ሥርዐቱንም ያከናውኑ ነበር።
20ከዚህም በኋላ እርሱ ወርዶ የእግዚአብሔርን በረከት በአንደበቱ ይሰጣቸው ዘንድ፥
በስሙም ይመኩ ዘንድ በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ላይ እጁን አነሣ።
21የልዑልንም በረከት ይቀበሉ ዘንድ ዳግመኛ ሰገዱ።
22አሁንም በሁሉም ቦታ ብዙ ተአምራት የሚያደርገውን፥
ከእናታችን ማኅፀን ጀምሮ ዘመናችንንም የሚያረዝመውን፥
እንደ ቸርነቱም ይቅርታውን የሚያደርግልንን፥ የሁሉን ፈጣሪ አመስግኑት።
23የልቡና ደስታንም ይሰጠናል፤
በዘመናችንም ሰላምን ያደርጋል፤ ለእስራኤልም ለዘለዓለም።
24በቸርነቱም ከእኛ ጋር የታመነ ነው፤
በዘመናችንም አዳነን።
25ሰውነቴ ሁለት ወገኖችን ጠላች፤
ሦስተኛው ግን ሕዝብ አይደለም።
26እነዚህም በሰማርያና በፍልስጥኤም ተራራ የሚኖሩ፥
በሰቂማ የሚኖሩ የአሞሬዎንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰነፎች ሕዝብ” ይላል። ሰዎች ናቸው።
27ጥበብን ከልቡ ያነቃት የኢየሩሳሌም ሰው የሲራክ አልዓዛር ልጅ
እኔ ኢያሱ የጥበብንና የምክርን ትምህርት በዚህ መጽሐፍ ጻፍሁ።
28ይህን እንደዚህ የሚያደርግ፥ በዚያም የሚራቀቅ ብፁዕ ነው፤
ይህንም በልቡ የሚጠብቀው ጠቢብ ይሆናል።
29ይህንም የሚያደርግ ሁሉን ይችላል፤
የእግዚአብሔር ብርሃን ይመራዋልና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 50: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 50
50
የኦንያ ልጅ ስምዖን
1የኦንያ ልጅ ታላቁ ካህን ስምዖንም
በሕይወቱ ቤተ መቅደስን አደሰ፤ በዘመኑም ቤተ መቅደስን አጸና።
2እንዲሁም የቅጥሩን መሠረት ዕጥፍ አድርጎ ሠራ
ካህን የሚለብሰውንም ቀጭን ልብስ ሠራ።
3በዘመኑም የውኃዎች ምንጮች አልጐደሉም፤
የጕድጓዱም ውኃ ብዛቱ እንደ ባሕር ውኃ ነበር።
4ሕዝቡም እንዳይወድቁ ይጠነቀቅላቸው ነበር፤
ከተማዋንም ከጠላት ለመከላከል መሸገ።
5ከቤተ መቅደስ መጋረጃ በወጣ ጊዜም በሕዝቡ መካከል ተከበረ።
6በደመና ውስጥ እንደ አጥቢያ ኮከብና
በምልዐት ቀን እንደ ሙሉ ጨረቃ ነበረ።
7በልዑል መቅደስም ላይ እንደምታበራ ፀሐይ ነበረ።
በብሩህ ደመናም ውስጥ ብርሃን እንደሚሰጥ ቀስተ ደመና ነበር።
8እንደ መጸው ወራት ጽጌረዳም ነበር፤
በውኃ መፍሰሻ አጠገብ እንደሚያፈራ አበባም ነበር፤
በመከርም ወራት እንደ ሊባኖስ ዛፍ ቅርንጫፍ ነበር።
9በጥና እሳት ላይ እንዳለ ነጭ ዕጣንም ነበር።
ተመትቶ እንደ ተሠራ የወርቅ ዕቃም ነበር።
በጌጥ ላይ እንዳለ የከበረ ዕንቍም ነበር፤
10ፍሬዋ ብዙ እንደ ሆነ የዘይት እንጨት፥
ከደመና በታች እንደሚያድግ የዋንዛ ዛፍ ነበር።
11እርሱም የክብር ልብሱን በለበሰ ጊዜ፥
የመመኪያውንም ጌጥ በለበሰ ጊዜ፥
ወደ ተቀደሰውም መሠዊያ በወጣ ጊዜ፥
በቅድስና ልብሱ ተከበረ።
12ከካህናቱም እጅ የመሥዋዕቱን ሥጋ ክፍል በተቀበለ ጊዜ፥
በመሠዊያው አጠገብ ይቆም ነበር፤
ወንድሞቹም በዙሪያው ቁመው ይጋርዱት ነበር፤
እንደ ሊባኖስ ለጋ ዝግባና እንደ ዘንባባም ዛፍ ይከቡት ነበር።
13እንዲሁም የአሮን ልጆች ሁሉ የክብር ልብሳቸውን ለብሰው፥
የእግዚአብሔርን መባእ በእጃቸው ይዘው፥
በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ፊት ይቆሙ ነበር።
14በመሠዊያውም ሥራቸውን ይፈጽሙ ነበር፤
ሁሉን የሚችል የልዑልንም መሥዋዕት ያዘጋጁ ነበር።
15የወይኑን ጽዋዕ ይዞ እጁን አነሣ፤
የወይኑን ዘለላ ደምም አፈሰሰ፤
ለንጉሠ ነገሥት ለልዑል በጎ መዓዛ አድርጎ
በመሠዊያው እግር ሥር ያፈስሰው ነበር።
16የአሮንም ልጆች እየጮሁ ምስጋናውን ይናገሩ ነበር፤
ተመትቶ የተሠራ የብር መለከትንም ይነፉ ነበር፤
በልዑልም ፊት ማሰባሰቢያ ሊሆን ቃላቸውን ያሰሙ ነበር።
17ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ያርፉ ነበር፤
በምድር ላይም በግንባራቸው ይሰግዱ ነበር፤
ሁሉን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርቡ ነበር።
18መዘምራኑም በቃላቸው ያመሰግኑት ነበር፥
የዜማቸውም ድምፅ ቤቱን ያስተጋባው ነበር።
19ሕዝቡም ወደ ልዑል እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር፤
በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ሥርዐቱን እስኪጨርሱ ድረስ
ይቅር በሚል በእግዚአብሔር ፊት ይለምኑ ነበር፤ ሥርዐቱንም ያከናውኑ ነበር።
20ከዚህም በኋላ እርሱ ወርዶ የእግዚአብሔርን በረከት በአንደበቱ ይሰጣቸው ዘንድ፥
በስሙም ይመኩ ዘንድ በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ላይ እጁን አነሣ።
21የልዑልንም በረከት ይቀበሉ ዘንድ ዳግመኛ ሰገዱ።
22አሁንም በሁሉም ቦታ ብዙ ተአምራት የሚያደርገውን፥
ከእናታችን ማኅፀን ጀምሮ ዘመናችንንም የሚያረዝመውን፥
እንደ ቸርነቱም ይቅርታውን የሚያደርግልንን፥ የሁሉን ፈጣሪ አመስግኑት።
23የልቡና ደስታንም ይሰጠናል፤
በዘመናችንም ሰላምን ያደርጋል፤ ለእስራኤልም ለዘለዓለም።
24በቸርነቱም ከእኛ ጋር የታመነ ነው፤
በዘመናችንም አዳነን።
25ሰውነቴ ሁለት ወገኖችን ጠላች፤
ሦስተኛው ግን ሕዝብ አይደለም።
26እነዚህም በሰማርያና በፍልስጥኤም ተራራ የሚኖሩ፥
በሰቂማ የሚኖሩ የአሞሬዎንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰነፎች ሕዝብ” ይላል። ሰዎች ናቸው።
27ጥበብን ከልቡ ያነቃት የኢየሩሳሌም ሰው የሲራክ አልዓዛር ልጅ
እኔ ኢያሱ የጥበብንና የምክርን ትምህርት በዚህ መጽሐፍ ጻፍሁ።
28ይህን እንደዚህ የሚያደርግ፥ በዚያም የሚራቀቅ ብፁዕ ነው፤
ይህንም በልቡ የሚጠብቀው ጠቢብ ይሆናል።
29ይህንም የሚያደርግ ሁሉን ይችላል፤
የእግዚአብሔር ብርሃን ይመራዋልና።