መጽ​ሐፈ ሲራክ 50

50
የኦ​ንያ ልጅ ስም​ዖን
1የኦ​ንያ ልጅ ታላቁ ካህን ስም​ዖ​ንም
በሕ​ይ​ወቱ ቤተ መቅ​ደ​ስን አደሰ፤ በዘ​መ​ኑም ቤተ መቅ​ደ​ስን አጸና።
2እን​ዲ​ሁም የቅ​ጥ​ሩን መሠ​ረት ዕጥፍ አድ​ርጎ ሠራ
ካህን የሚ​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ቀጭን ልብስ ሠራ።
3በዘ​መ​ኑም የው​ኃ​ዎች ምን​ጮች አል​ጐ​ደ​ሉም፤
የጕ​ድ​ጓ​ዱም ውኃ ብዛቱ እንደ ባሕር ውኃ ነበር።
4ሕዝ​ቡም እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ ይጠ​ነ​ቀ​ቅ​ላ​ቸው ነበር፤
ከተ​ማ​ዋ​ንም ከጠ​ላት ለመ​ከ​ላ​ከል መሸገ።
5ከቤተ መቅ​ደስ መጋ​ረጃ በወጣ ጊዜም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ተከ​በረ።
6በደ​መና ውስጥ እንደ አጥ​ቢያ ኮከ​ብና
በም​ል​ዐት ቀን እንደ ሙሉ ጨረቃ ነበረ።
7በል​ዑል መቅ​ደ​ስም ላይ እን​ደ​ም​ታ​በራ ፀሐይ ነበረ።
በብ​ሩህ ደመ​ናም ውስጥ ብር​ሃን እን​ደ​ሚ​ሰጥ ቀስተ ደመና ነበር።
8እንደ መጸው ወራት ጽጌ​ረ​ዳም ነበር፤
በውኃ መፍ​ሰሻ አጠ​ገብ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ አበ​ባም ነበር፤
በመ​ከ​ርም ወራት እንደ ሊባ​ኖስ ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ ነበር።
9በጥና እሳት ላይ እን​ዳለ ነጭ ዕጣ​ንም ነበር።
ተመ​ትቶ እንደ ተሠራ የወ​ርቅ ዕቃም ነበር።
በጌጥ ላይ እን​ዳለ የከ​በረ ዕን​ቍም ነበር፤
10ፍሬዋ ብዙ እንደ ሆነ የዘ​ይት እን​ጨት፥
ከደ​መና በታች እን​ደ​ሚ​ያ​ድግ የዋ​ንዛ ዛፍ ነበር።
11እር​ሱም የክ​ብር ልብ​ሱን በለ​በሰ ጊዜ፥
የመ​መ​ኪ​ያ​ው​ንም ጌጥ በለ​በሰ ጊዜ፥
ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ውም መሠ​ዊያ በወጣ ጊዜ፥
በቅ​ድ​ስና ልብሱ ተከ​በረ።
12ከካ​ህ​ና​ቱም እጅ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ሥጋ ክፍል በተ​ቀ​በለ ጊዜ፥
በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ይቆም ነበር፤
ወን​ድ​ሞ​ቹም በዙ​ሪ​ያው ቁመው ይጋ​ር​ዱት ነበር፤
እንደ ሊባ​ኖስ ለጋ ዝግ​ባና እንደ ዘን​ባ​ባም ዛፍ ይከ​ቡት ነበር።
13እን​ዲ​ሁም የአ​ሮን ልጆች ሁሉ የክ​ብር ልብ​ሳ​ቸ​ውን ለብ​ሰው፥
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባእ በእ​ጃ​ቸው ይዘው፥
በእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ፊት ይቆሙ ነበር።
14በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ሥራ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ነበር፤
ሁሉን የሚ​ችል የል​ዑ​ል​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያዘ​ጋጁ ነበር።
15የወ​ይ​ኑን ጽዋዕ ይዞ እጁን አነሣ፤
የወ​ይ​ኑን ዘለላ ደምም አፈ​ሰሰ፤
ለን​ጉሠ ነገ​ሥት ለል​ዑል በጎ መዓዛ አድ​ርጎ
በመ​ሠ​ዊ​ያው እግር ሥር ያፈ​ስ​ሰው ነበር።
16የአ​ሮ​ንም ልጆች እየ​ጮሁ ምስ​ጋ​ና​ውን ይና​ገሩ ነበር፤
ተመ​ትቶ የተ​ሠራ የብር መለ​ከ​ት​ንም ይነፉ ነበር፤
በል​ዑ​ልም ፊት ማሰ​ባ​ሰ​ቢያ ሊሆን ቃላ​ቸ​ውን ያሰሙ ነበር።
17ያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ያርፉ ነበር፤
በም​ድር ላይም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ይሰ​ግዱ ነበር፤
ሁሉን ለሚ​ገዛ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምስ​ጋና ያቀ​ርቡ ነበር።
18መዘ​ም​ራ​ኑም በቃ​ላ​ቸው ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር፥
የዜ​ማ​ቸ​ውም ድምፅ ቤቱን ያስ​ተ​ጋ​ባው ነበር።
19ሕዝ​ቡም ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ጸን​ተው ሥር​ዐ​ቱን እስ​ኪ​ጨ​ርሱ ድረስ
ይቅር በሚል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​ምኑ ነበር፤ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ያከ​ና​ውኑ ነበር።
20ከዚ​ህም በኋላ እርሱ ወርዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ከት በአ​ን​ደ​በቱ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥
በስ​ሙም ይመኩ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ላይ እጁን አነሣ።
21የል​ዑ​ል​ንም በረ​ከት ይቀ​በሉ ዘንድ ዳግ​መኛ ሰገዱ።
22አሁ​ንም በሁ​ሉም ቦታ ብዙ ተአ​ም​ራት የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን፥
ከእ​ና​ታ​ችን ማኅ​ፀን ጀምሮ ዘመ​ና​ች​ን​ንም የሚ​ያ​ረ​ዝ​መ​ውን፥
እንደ ቸር​ነ​ቱም ይቅ​ር​ታ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ንን፥ የሁ​ሉን ፈጣሪ አመ​ስ​ግ​ኑት።
23የል​ቡና ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ናል፤
በዘ​መ​ና​ች​ንም ሰላ​ምን ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም።
24በቸ​ር​ነ​ቱም ከእኛ ጋር የታ​መነ ነው፤
በዘ​መ​ና​ች​ንም አዳ​ነን።
25ሰው​ነቴ ሁለት ወገ​ኖ​ችን ጠላች፤
ሦስ​ተ​ኛው ግን ሕዝብ አይ​ደ​ለም።
26እነ​ዚ​ህም በሰ​ማ​ር​ያና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ተራራ የሚ​ኖሩ፥
በሰ​ቂማ የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰነ​ፎች ሕዝብ” ይላል። ሰዎች ናቸው።
27ጥበ​ብን ከልቡ ያነ​ቃት የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰው የሲ​ራክ አል​ዓ​ዛር ልጅ
እኔ ኢያሱ የጥ​በ​ብ​ንና የም​ክ​ርን ትም​ህ​ርት በዚህ መጽ​ሐፍ ጻፍሁ።
28ይህን እን​ደ​ዚህ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በዚ​ያም የሚ​ራ​ቀቅ ብፁዕ ነው፤
ይህ​ንም በልቡ የሚ​ጠ​ብ​ቀው ጠቢብ ይሆ​ናል።
29ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉን ይች​ላል፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን ይመ​ራ​ዋ​ልና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ