መጽሐፈ ጥበብ 1
1
ትክክለኛ ፍርድን ስለ መሻት
1የምድር ገዥዎች ሆይ፥ ጽድቅን ውደዷት፥ የእግዚአብሔርንም ኀይል በበጎ ዕውቀት አስቡት፥ በቅን ልቡናም ፈልጉት። 2በማይፈታተኑት ሰዎች ዘንድ እርሱ ይገኛልና። በማይክዱት ሰዎችም ዘንድ ይገለጣልና። 3ጠማማ አሳብ ከእግዚአብሔር ያርቃል፤ የተፈተነችም ኀይል አላዋቂዎችን ትዘልፋቸዋለች።
4በተተነኰለች ሰውነት ጥበብ አትገባምና፤ ለኀጢአት በተገዛ ሰውነትም አታድርምና። 5ተግሣጽን የሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ ክፉውን ትምህርት ያርቃልና፥ ከሰነፎችም ልቡና ድል ነሥቶ ይሄዳልና በሚመጣም ጊዜ ክፉውን ይዘልፈዋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ይለያል። 6ጥበብን የሚገልጽ መንፈስ ሰው ወዳጅ ነውና፥ በከንፈሩ የሚሳደበውንም አያነጻውም። እግዚአብሔር በኵላሊቶቹ ምስክር ነውና፥ ነዋሪ ጕበኛም ልቡናውን ይመረምረዋል፤ አንደበቱንም ይሰማዋል። 7የእግዚአብሔር መንፈስ ዓለሙን መልትዋልና። ዓለምንም ሁሉ የያዘው እርሱ ነገራቸውን ፈጽሞ ያውቃልና። 8ስለዚህ ከሚነገር ከዐመፃ ነገራቸው ምንም ከእርሱ አይሰወርም። ሥራውን በመግለጥ ፍርዱ አይተላለፈውምና። 9ክፉዎችን በልቡናቸው ምክር ይመረምራቸዋልና፥ የነገራቸውም ድምፅ ለበደላቸው ዘለፋ ሊሆንባቸው ወደ እግዚአብሔር ይደርሳልና። 10#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የቅናት ጆሮ ሁሉን ይሰማል” ይላል። ስለ ቅንአት ሥራውን ሁሉ የሚሰማ አይደለምና፥ የነጐርጓርም ድምፅ ከእርሱ አይሰወርም። 11ከማይረባ ነጐርጓር ተጠበቁ፤ ከሐሜትም አንደበታችሁን ከልክሉ፤ በስውር የሚሆን ነገር በከንቱ አይወጣምና፥ የሚወጋና የሚዋሽ አፍ ሰውን ይገድላልና።
እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረም
12በሕይወታችሁ ስሕተት ለሞት አትቅኑ፤ በእጃችሁም ሥራ ጥፋትን አታምጡ። 13እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና፤ የሕያዋንም ጥፋት ደስ አያሰኘውምና። 14ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረቱን ፈጥሮአልና፥ የዓለም መፈጠርም ለድኅነት ነውና፥ በእነርሱም ዘንድ የጥፋት መርዝ አልነበረምና፥ ለሲኦልም በምድር ላይ ግዛት አልነበረውምና። 15ጽድቅ አትሞትምና። 16ክፉዎች ግን በእጃቸውና በቃላቸው ጠሩት፥ ባልንጀራም አስመሰሉት። በእርሱም ጠፉ። 17የእርሱ ወገን መሆን ይገባቸዋልና ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጥበብ 1: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ