መጽ​ሐፈ ተግ​ሣጽ 6

6
1 # በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ምዕ. 31 ከቍ. 10 እስከ 31 ያለው ነው። ልባም ሴትን ማን ያገ​ኛ​ታል?
ዋጋው ብዙ ከሆነ ከከ​በረ ዕንቍ እጅግ የከ​በ​ረች ናት።
2እን​ደ​ዚህ ባለ​ችዋ ሴት የባ​ልዋ ልብ ይታ​መ​ን​ባ​ታል፥
እን​ዲህ ያለ​ችው ሴትም ከመ​ል​ካም ምርኮ አታ​ሳ​ን​ሰ​ውም።
3ዕድ​ሜ​ዋን ሙሉ በክፉ ላይ ክፉ ያይ​ደለ፥
በበጎ ላይ በጎ እየ​ሠ​ራች ባሏን ትረ​ዳ​ዋ​ለች።
4የበግ ጠጕ​ር​ንና የተ​ልባ እግ​ርን እያ​ባ​ዘ​ተች፥
በእ​ጆ​ችዋ መል​ካም ትሠ​ራ​ለች።
5እር​ስዋ ከሩቅ እን​ደ​ም​ት​ነ​ግድ፥
ሀብ​ት​ንም ሁሉ እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ መር​ከብ ናት፤
6ገና ሌሊት ሳለ ትነ​ሣ​ለች፤
ለቤተ ሰዎ​ችዋ ምግ​ባ​ቸ​ውን ትሰ​ጣ​ለች።
ለገ​ረ​ዶ​ች​ዋም ተግ​ባ​ራ​ቸ​ውን ትሰ​ጣ​ለች።
7እር​ሻ​ንም ተመ​ል​ክታ ትገ​ዛ​ለች፤
ከእ​ጅ​ዋም ፍሬ ወይ​ንን ትተ​ክ​ላ​ለች።
8ወገ​ብ​ዋ​ንም በኀ​ይል ትታ​ጠ​ቃ​ለች፥
እጆ​ች​ዋ​ንም ለሥራ ታወ​ጣ​ለች።
9ሥራ መል​ካም እንደ ሆነ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለች፤
መብ​ራቷ ሌሊ​ቱን ሁሉ አይ​ጠ​ፋም።
10እጆ​ች​ዋ​ንም ወደ​ሚ​ጠ​ቅም ሥራ ትዘ​ረ​ጋ​ለች፥
ክን​ድ​ዋ​ንም ለመ​ፍ​ተል ታበ​ረ​ታ​ለች።
11እጅ​ዋን ለች​ግ​ረኛ ትዘ​ረ​ጋ​ለች፥
መሀል እጅ​ዋ​ንም ወደ ድሃ ትዘ​ረ​ጋ​ለች።
12ባሏ በውጭ የዘ​ገየ እንደ ሆነ በቤት ስላ​ሉት ምንም አያ​ስ​ብም ።
ቤተ ሰዎ​ችዋ ሁሉ እጥፍ ድርብ የለ​በሱ ናቸ​ውና።
13ለባሏ እጥፍ ሆኖ ከተ​ፈ​ተለ የተ​ልባ እግር መጐ​ና​ጸ​ፊያ ትሠ​ራ​ለች፤
ለራ​ስ​ዋም ከነጭ ሐር ልብ​ስን ትሠ​ራ​ለች።
14ባልዋ በሀ​ገር ሽማ​ግ​ሌ​ዎች መካ​ከል በሸ​ንጎ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ፥
በአ​ደ​ባ​ባይ የታ​ወቀ ይሆ​ናል።
15የበ​ፍታ ቀሚስ እየ​ሠ​ራች ትሸ​ጣ​ለች።
ለከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ድግ ትሸ​ጣ​ለች።
ሕጋዊ በሆነ ነገር አፍ​ዋን ትከ​ፍ​ታ​ለች፤
ለአ​ን​ደ​በ​ቷም መጠ​ንን ታደ​ር​ጋ​ለች።
16ብር​ታ​ት​ንና ውበ​ትን ትለ​ብ​ሳ​ለች፤
በኋ​ላም ዘመን ላይ ደስ ይላ​ታል።
17ወደ ቤትዋ የሚ​ገባ ብዙ ነው፥
የስ​ን​ፍና እን​ጀ​ራ​ንም አት​በ​ላም።
18ሕግና ምጽ​ዋት በአ​ፍዋ አለ፥
አፍ​ዋን በጥ​በ​ብና ሕግ ባለው ሥር​ዐት ትከ​ፍ​ታ​ለች።
19ምጽ​ዋቷ ልጆ​ች​ዋን ያሳ​ድ​ጋል፥ ያበ​ለ​ጥ​ጋ​ልም፤
ባል​ዋም እን​ዲህ ሲል ያመ​ሰ​ግ​ና​ታል፦
20“ብዙ ሴቶች ልጆች ሀብ​ትን ሰበ​ሰቡ፤
ብዙ​ዎ​ቹም ኀይ​ልን አደ​ረጉ፤
አንቺ ግን ትበ​ል​ጫ​ለሽ፥ ከሁ​ሉም ትል​ቂ​ያ​ለሽ።”
21ውበት ሐሰት ነው፥ ደም​ግ​ባ​ትም ከንቱ ነው፤
ብልህ ሴት ግን ትባ​ረ​ካ​ለች።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈራ እር​ስዋ ትመ​ሰ​ገ​ና​ለች።
22ከከ​ን​ፈሯ ፍሬ ስጡ​አት፥
ባሏም በአ​ደ​ባ​ባይ ይመ​ሰ​ገ​ናል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ