መጽሐፈ ተግሣጽ 5
5
1 # በዕብራይስጥና በግሪክ ሰባ. ሊ. ምሳሌ ምዕ. 29 ነው። አንገቱን ካደነደነ ሰው ይልቅ፥
የሚዘልፍ ሰው ይሻላል።
ድንገት ይቃጠላልና፥ፈውስም የለውምና።
2በጻድቃን መመስገን ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤
ክፉዎች ገዢዎች በሚሆኑበት ጊዜ ግን ሰዎች ያለቅሳሉ።
3ጥበብን በሚወድድ ልጅ አባቱ ደስ ይለዋል፤
ጋለሞቶችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያጠፋል።
4እውነተኛ ንጉሥ ሀገሩን ያጸናል፤
ዐመፀኛ ሰው ግን ያፈርሰዋል።
5በወዳጁ ፊት ወጥመድን የሚያዘጋጅ ሰው
የራሱን እግሮች በውስጡ ያገባል።
6በክፉ ሰው ዐመፃ ወጥመድ ይበዛል፤
ኀጢአተኛ ሰውም በታላቅ ወጥመድ ይወድቃል፥#“ኀጢአተኛ ሰውም በታላቅ ወጥመድ ይወድቃል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ጻድቅ ግን በደስታና በሐሴት ይኖራል።
7ጻድቅ የድሆችን ፍርድ ይመለከታል፤
ኃጥእ ግን ዕውቀትን አያስተውልም።
ለድሃም ዕውቀት ያለው ልቡና የለውም።
8ክፉዎች ሰዎች ከተማን ያቃጥላሉ፤
ጠቢባን ግን ቍጣን ይመልሳሉ።
9ጠቢብ ሰው ሕዝብን ይገዛል፥
ክፉ ሰው ግን ይቈጣል፥ ይሥቁበታልም፥
ነገር ግን አያሳዝነውም።
10ደምን ለማፍሰስ የሚተባበሩ ሰዎች ጻድቁን ሰው ይጠላሉ፥
ቅኖች ግን ነፍሱን ይሻሉ።
11አላዋቂ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤
ጠቢብ ሰው ግን ድርሻውን እንኳ በከፊል ያስቀረዋል።
12ንጉሥ ሐሰተኛ ነገርን ቢያደምጥ፥
በእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዐመፀኞች ይሆናሉ።
13አበዳሪና ተበዳሪ በተገናኙ ጊዜ
እግዚአብሔር ሁለቱን በአንድነት ይጐበኛቸዋል።
14ለድሆች በእውነት የሚፈርድ ንጉሥ፥
ዙፋኑ ለዘለዓለም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለምስክር” ይላል። ይጸናል።
15በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፤
ስሕተተኛ ብላቴና ግን ቤተ ሰቦቹን ያሳፍራል።
16ኃጥኣን ሲበዙ ኀጢአት ትበዛለች፤
ጻድቃን ግን በክፉዎች ውድቀት ይፈራሉ።
17ልጅህን ቅጣ፥ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፤
ለነፍስህም ክብርን ይሰጣታል።
18ለኀጢአተኛ ሕዝብ አስተማሪ የለውም፤
ሕግን የሚጠብቅ ግን ብፁዕ ነው።
19ክፉ አገልጋይ በቃል አይገሠጽም፤
ቢያውቅ እንኳ አይታዘዝምና።
20በቃሉ የሚቸኩለውን ሰው ብታይ፥
ከእርሱ ይልቅ ለአላዋቂ ተስፋ እንዳለ ዕወቅ።
21ቸልተኛ ሰው ከሕፃንነቱ ጀምሮ አገልጋይ ይሆናል፤
በኋላ ግን ራሱን ያሳዝናል።
22ቍጡ ሰው ጠብን ይጭራል፥
ወፈፍተኛ ሰውም ኀጢአትን ያበዛል።
23ትዕቢት ሰውን ያዋርደዋል፥
ሕሊናውን የሚያዋርደውን ሰው ግን እግዚአብሔር ለክብር ያቀርበዋል።
24ከሌባ ጋር የሚካፈል ነፍሱን ይጠላል፤
መሐላንም ቢያወርዱለት ይምላል፤ አይናገርምም።
25በመፍራትና በማፈር ሰው ይሰነካከላል፤
በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ደስ ይለዋል።
የሰው ኀጢአቱ በደለኛ ያሰኘዋል፥
በእግዚአብሔር የታመነ ሰው ግን ይድናል።
26ብዙ ሰዎች ለመኳንንት ፊት ይላላካሉ፤
የሰው ፍርዱ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
27እውነተኛ ሰው በግፈኛ ሰው ዘንድ የተናቀ ነው፤
ቀና መንገድም በኃጥኣን ዘንድ አስጸያፊ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ተግሣጽ 5: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ተግሣጽ 5
5
1 # በዕብራይስጥና በግሪክ ሰባ. ሊ. ምሳሌ ምዕ. 29 ነው። አንገቱን ካደነደነ ሰው ይልቅ፥
የሚዘልፍ ሰው ይሻላል።
ድንገት ይቃጠላልና፥ፈውስም የለውምና።
2በጻድቃን መመስገን ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤
ክፉዎች ገዢዎች በሚሆኑበት ጊዜ ግን ሰዎች ያለቅሳሉ።
3ጥበብን በሚወድድ ልጅ አባቱ ደስ ይለዋል፤
ጋለሞቶችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያጠፋል።
4እውነተኛ ንጉሥ ሀገሩን ያጸናል፤
ዐመፀኛ ሰው ግን ያፈርሰዋል።
5በወዳጁ ፊት ወጥመድን የሚያዘጋጅ ሰው
የራሱን እግሮች በውስጡ ያገባል።
6በክፉ ሰው ዐመፃ ወጥመድ ይበዛል፤
ኀጢአተኛ ሰውም በታላቅ ወጥመድ ይወድቃል፥#“ኀጢአተኛ ሰውም በታላቅ ወጥመድ ይወድቃል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
ጻድቅ ግን በደስታና በሐሴት ይኖራል።
7ጻድቅ የድሆችን ፍርድ ይመለከታል፤
ኃጥእ ግን ዕውቀትን አያስተውልም።
ለድሃም ዕውቀት ያለው ልቡና የለውም።
8ክፉዎች ሰዎች ከተማን ያቃጥላሉ፤
ጠቢባን ግን ቍጣን ይመልሳሉ።
9ጠቢብ ሰው ሕዝብን ይገዛል፥
ክፉ ሰው ግን ይቈጣል፥ ይሥቁበታልም፥
ነገር ግን አያሳዝነውም።
10ደምን ለማፍሰስ የሚተባበሩ ሰዎች ጻድቁን ሰው ይጠላሉ፥
ቅኖች ግን ነፍሱን ይሻሉ።
11አላዋቂ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤
ጠቢብ ሰው ግን ድርሻውን እንኳ በከፊል ያስቀረዋል።
12ንጉሥ ሐሰተኛ ነገርን ቢያደምጥ፥
በእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዐመፀኞች ይሆናሉ።
13አበዳሪና ተበዳሪ በተገናኙ ጊዜ
እግዚአብሔር ሁለቱን በአንድነት ይጐበኛቸዋል።
14ለድሆች በእውነት የሚፈርድ ንጉሥ፥
ዙፋኑ ለዘለዓለም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለምስክር” ይላል። ይጸናል።
15በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፤
ስሕተተኛ ብላቴና ግን ቤተ ሰቦቹን ያሳፍራል።
16ኃጥኣን ሲበዙ ኀጢአት ትበዛለች፤
ጻድቃን ግን በክፉዎች ውድቀት ይፈራሉ።
17ልጅህን ቅጣ፥ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፤
ለነፍስህም ክብርን ይሰጣታል።
18ለኀጢአተኛ ሕዝብ አስተማሪ የለውም፤
ሕግን የሚጠብቅ ግን ብፁዕ ነው።
19ክፉ አገልጋይ በቃል አይገሠጽም፤
ቢያውቅ እንኳ አይታዘዝምና።
20በቃሉ የሚቸኩለውን ሰው ብታይ፥
ከእርሱ ይልቅ ለአላዋቂ ተስፋ እንዳለ ዕወቅ።
21ቸልተኛ ሰው ከሕፃንነቱ ጀምሮ አገልጋይ ይሆናል፤
በኋላ ግን ራሱን ያሳዝናል።
22ቍጡ ሰው ጠብን ይጭራል፥
ወፈፍተኛ ሰውም ኀጢአትን ያበዛል።
23ትዕቢት ሰውን ያዋርደዋል፥
ሕሊናውን የሚያዋርደውን ሰው ግን እግዚአብሔር ለክብር ያቀርበዋል።
24ከሌባ ጋር የሚካፈል ነፍሱን ይጠላል፤
መሐላንም ቢያወርዱለት ይምላል፤ አይናገርምም።
25በመፍራትና በማፈር ሰው ይሰነካከላል፤
በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ደስ ይለዋል።
የሰው ኀጢአቱ በደለኛ ያሰኘዋል፥
በእግዚአብሔር የታመነ ሰው ግን ይድናል።
26ብዙ ሰዎች ለመኳንንት ፊት ይላላካሉ፤
የሰው ፍርዱ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
27እውነተኛ ሰው በግፈኛ ሰው ዘንድ የተናቀ ነው፤
ቀና መንገድም በኃጥኣን ዘንድ አስጸያፊ ነው።