መጽ​ሐፈ ተግ​ሣጽ 4

4
1 # በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምሳሌ ምዕ. 28 ነው። ኃጥእ ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ደው ይሸ​ሻል፤
ጻድቅ ግን እንደ አን​በሳ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል።
2በክ​ፉ​ዎች በደል መቅ​ሠ​ፍት ይነ​ሣል፤
ዐዋቂ ሰው ግን ፈጽሞ ያጠ​ፋ​ዋል።
3በኀ​ጢ​አት የጸና ሰው ድሆ​ችን ይቀ​ማል፤
እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም እንደ ከባድ ዝና​ብም ነው፥
4ሕግን የሚ​ተ​ዉና ኀጢ​አ​ትን የሚ​ያ​ወ​ድሱ እን​ደ​ዚሁ ናቸው።
ሕግ ጠባ​ቂ​ዎች ግን ለራ​ሳ​ቸው ቅጥ​ርን ይሠ​ራሉ።
5ክፉ​ዎች ሰዎች ፍር​ድን አያ​ስ​ተ​ው​ሉም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚሹ ግን ሁሉን ያስ​ተ​ው​ላሉ።
6ከሐ​ሰ​ተኛ ባለ​ጠጋ፥
በእ​ው​ነት የሚ​ሄድ ድሃ ይሻ​ላል።
7ሕግን የሚ​ጠ​ብቅ ልጅ ዐዋቂ ነው፤
አመ​ን​ዝራ ሴትን የሚ​መ​ለ​ከት ግን ለጥ​ፋት ይዳ​ረ​ጋል፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለጥ​ፋት ይዳ​ረ​ጋል” አይ​ልም።
አባ​ቱ​ንም ያሰ​ድ​ባል።
8በአ​ራ​ጣና በቅ​ሚያ ሀብ​ቱን የሚ​ያ​በዛ
ለድሃ ለሚ​ራራ ያከ​ማ​ች​ለ​ታል።
9ሕግን ከመ​ስ​ማት ጆሮ​ውን የሚ​መ​ልስ ሰው
ጸሎቱ የተ​ናቀ ነው።
10ቅኖ​ችን#አን​ዳ​ንድ የግ​እዝ ዘርዕ “ዕው​ራ​ንን” ይላል። በክፉ መን​ገድ የሚ​ያ​ስት፥
እርሱ ወደ ጥፋት ይወ​ድ​ቃል፤
ዐመ​ፀ​ኞች ግን በመ​ል​ካም በኩል ያል​ፋሉ፥
ወደ ውስ​ጧም አይ​ገ​ቡም።
11ባለ​ጠጋ ሰው ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመ​ስ​ለ​ዋል፤
አስ​ተ​ዋይ ድሃ ግን ይመ​ረ​ም​ረ​ዋል።
12በጻ​ድ​ቃን ረድ​ኤት ብዙ ክብር አለ፤
በኃ​ጥ​ኣን መን​ገድ ግን ሰዎች ይጠ​ፋሉ።
13በደ​ሉን የሚ​ሰ​ውር ሰው መን​ገዱ አይ​ቃ​ናም፤
የሚ​ና​ዘ​ዝና ራሱን የሚ​ዘ​ልፍ ግን ይወ​ደ​ዳል።
14ስለ ጽድቅ ሁል​ጊዜ የሚ​ደ​ነ​ግጥ ሰው ብፁዕ ነው፤
ልቡን የሚ​ያ​ጸና ግን በክፉ ይወ​ድ​ቃል።
15ራሱ ድሃ ሆኖ ሳለ ድሃ ሕዝ​ብን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ክፉ መኰ​ንን፥
እንደ ተራበ አን​በ​ሳና እንደ ተጠማ ተኵላ ነው።
16አእ​ምሮ የጐ​ደ​ለው ንጉሥ ብዙ ግብ​ርን አስ​ገ​ባሪ ይሆ​ናል፤
ግፍን የሚ​ጠላ ግን ብዙ ዘመን ይኖ​ራል።
17በሰው ደም የሚ​ገባ ዐመ​ፀኛ ሰው
ወደ ጕድ​ጓድ በሚ​ገ​ባ​በት ጊዜ የሚ​ይ​ዘው የለም፥#“በሰው ደም የሚ​ገባ ዐመ​ፀኛ ሰው ወደ ጕድ​ጓድ በሚ​ገ​ባ​በት ጊዜ የሚ​ይ​ዘው የለም” የሚ​ለ​ውን ግእዙ ከዕ​ብ​ራ​ይ​ስጡ የወ​ሰ​ደው ነው።
ለነ​ፍሰ ገዳ​ይም ዋስ የሚ​ሆን ሰው ይሰ​ደ​ዳል፥
በደ​ኅ​ናም አይ​ኖ​ርም።
ልጅ​ህን አስ​ተ​ም​ረው ይወ​ድ​ድ​ሃ​ልም፥
ለነ​ፍ​ስ​ህም ክብ​ርን ይሰ​ጣል።
ዐመ​ፀኛ ሕዝብ ሕግን አይ​ሰ​ማም።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ የለም።
18በጽ​ድቅ መን​ገድ የሚ​ሄድ ሰው ይረ​ዳል፥
በጠ​ማማ መን​ገድ የሚ​ሄድ ግን በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል።
19ምድ​ሩን የሚ​ያ​ርስ እን​ጀ​ራን ይጠ​ግ​ባል፤
ሥራ ፈት​ነ​ትን የሚ​ያ​በዛ ግን ድህ​ነ​ትን ያበ​ዛል።
20የታ​መነ ሰው እጅግ ይባ​ረ​ካል፤
ክፉ ሰው ግን ከቅ​ጣት አይ​ድ​ንም።
21የጻ​ድ​ቃ​ንን ፊት የማ​ያ​ፍር ሰው ደግ አይ​ደ​ለም፥
እን​ዲህ ያለ ሰው በቍ​ራሽ እን​ጀራ ሰውን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።
22ምቀኛ ሰው ባለ​ጠጋ ለመ​ሆን ይቸ​ኩ​ላል፥
የሚ​ራራ ሰውም እን​ደ​ሚ​ገ​ዛው አያ​ው​ቅም።
23በም​ላሱ ከሚ​ሸ​ነ​ግል ሰው ይልቅ
የሰ​ውን መን​ገድ የሚ​ነ​ቅፍ እጅግ ክብ​ርን ያገ​ኛል።
24ከአ​ባ​ቱና ከእ​ናቱ የሚ​ሰ​ርቅ፥
ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም የሚል፥
የአ​ጥፊ ባል​ን​ጀራ ነው።
25የሚ​ሳሳ ሰው ከን​ቱን ይፈ​ር​ዳል፤
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መን ግን በጥ​ን​ቃቄ ይኖ​ራል።
26በልቡ ደስታ የሚ​ታ​መን ሰው እን​ደ​ዚሁ ሰነፍ ነው፤
በጥ​በብ የሚ​ሄድ ግን ይድ​ናል።
27ለድሃ የሚ​ሰጥ አይ​ቸ​ገ​ርም፤
ዐይ​ኖ​ቹን የሚ​ያ​ዞር ግን በከ​ባድ ችግር ይኖ​ራል።
28በኃ​ጥ​ኣን ቦታ ጻድ​ቃን ያለ​ቅ​ሳሉ፥
በእ​ነ​ርሱ ጥፋት ግን ጻድ​ቃን ይበ​ዛሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ