መኃልየ መኃልይ 4
4
1ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥
እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥
በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፥
ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ
እንደ ፍየል መንጋ ነው።
2ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ተሸለቱ
ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ
ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።
3ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥
አፍሽም ያማረ ነው፥
በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ
እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
4አንገትሽ ለሰልፍ ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራው እንደ ዳዊት ግንብ ነው፥
ሺህ ጋሻ የኃያላንም መሣሪያ ሁሉ ተንጠልጥሎበታል።
5ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ እንደ ተወለዱ፥
በሱፍ አበባ መካከል እንደሚሰማሩ
እንደ ሚዳቋ ግልገሎች ናቸው።
6ቀኑ እስኪነፍስ ጥላውም እስኪያልፍ ድረስ፥
ወደ ከርቤው ተራራ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ።
7ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥
ነውርም የለብሽም።
8ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥
ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥
ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥
ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።
9እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ልቤን በደስታ አሳበድሽው፥
አንድ ጊዜ በዓይኖችሽ፥ ከአንገትሽስ ድሪ በአንዱ
ልቤን በደስታ አሳበድሽው።
10እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው!
ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል!
የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ! 11ሙሽራዬ ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ ማር ይንጠበጠባል፥
ከምላስሽ በታች ማርና ወተት አለ፥
የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።
12እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥
የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።
13ቡቃያሽ ሮማንና የተመረጠ ፍሬ፥
ቆዕ ከናርዶስ ጋር ያለበት ገነት ነው፥
14ናርዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረፋ፥
ከልዩ ልዩ ዕጣን ጋር፥
ከርቤና እሬት ከክቡር ሽቱ ሁሉ ጋር።
15አንቺ የገነት ምንጭ፥ የሕይወት ውኃ ጕድጓድ፥
ከሊባኖስም የሚፈስስ ወንዝ ነሽ።
16የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥
የደቡብም ነፋስ ና፥
በገነቴ ላይ ንፈስ፥
ሽቱውም ይፍሰስ፥
ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ
መልካሙንም ፍሬ ይብላ።
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ 4: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ