1 ዜና መዋዕል 10:13-14 - Compare All Versions
1 ዜና መዋዕል 10:13-14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪን ጠየቀ። ነቢዩ ሳሙኤልም መለሰለት፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ ዘንድ አልሰማውም፥ ስለዚህ ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።
1 ዜና መዋዕል 10:13-14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ሳኦል ለእግዚአብሔር ስላልታመነ ሞተ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልጠበቀም፤ ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤ ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።
1 ዜና መዋዕል 10:13-14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።
1 ዜና መዋዕል 10:13-14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ሳኦል ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ሞተ፤ እርሱ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጸመም፤ እንዲያውም የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን በመጠየቅ መመሪያ ለማግኘት ሞከረ እንጂ እግዚአብሔርን አልጠየቀም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አስተላለፈ።
1 ዜና መዋዕል 10:13-14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እንዲሁ ሳኦል በጌታ ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የጌታንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ፥ ጌታንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አስተላለፈ።