ኤፌሶን 2:8-10
ኤፌሶን 2:8-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አምነን በጸጋው ድነናልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ የእናንተ ሥራ አይደለም። የሚመካም እንዳይኖር በምግባራችን አይደለም። እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ላዘጋጀው በጎ ሥራ በኢየሱስ ክርስቶስ የፈጠረን ፍጥረቱ ነንና።
Share
ኤፌሶን 2 ያንብቡኤፌሶን 2:8-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤ ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድንመላለስባቸው ያዘጋጀልንን መልካም የሆኑትን ሥራዎች እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።
Share
ኤፌሶን 2 ያንብቡኤፌሶን 2:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም። ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
Share
ኤፌሶን 2 ያንብቡኤፌሶን 2:8-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እናንተ የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋው ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በእናንተ ሥራ የተገኘ አይደለም። ማንም ሰው እንዳይመካ፥ የመዳን ጸጋ የተገኘው በሥራ አይደለም፤ እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።
Share
ኤፌሶን 2 ያንብቡ