ዘፍጥረት 8:1-22

ዘፍጥረት 8:1-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤ የቀ​ላ​ዩም ምን​ጮች፥ የሰ​ማ​ይም መስ​ኮ​ቶች ተደ​ፈኑ፤ ዝና​ብም ከሰ​ማይ ተከ​ለ​ከለ፤ ውኃ​ውም ከም​ድር ላይ እያ​ደር እየ​ቀ​ለለ ይሄድ ጀመረ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጐደለ። መር​ከ​ቢ​ቱም በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን በአ​ራ​ራት ተራ​ሮች ላይ ተቀ​መ​ጠች። ውኃ​ውም እስከ ዐሥ​ረ​ኛው ወር ድረስ ይጐ​ድል ነበር፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የተ​ራ​ሮቹ ራሶች ተገ​ለጡ። ከአ​ርባ ቀን በኋ​ላም ኖኅ የሠ​ራ​ውን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን መስ​ኮት ከፈተ፤ ከም​ድ​ርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እን​ደ​ሆነ ያይ ዘንድ ቁራ​ውን ላከው፤ እር​ሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከም​ድር ላይ እስ​ኪ​ደ​ርቅ ድረስ አል​ተ​መ​ለ​ሰም። ርግ​ብ​ንም ውኃው ከም​ድር ፊት ጐድሎ እንደ ሆነ እን​ድ​ታይ ከእ​ርሱ በኋላ ላካት። ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት። ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን እን​ደ​ገና ከመ​ር​ከብ ላካት። ርግ​ብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ በአ​ፍ​ዋም እነሆ፥ የለ​መ​ለመ የወ​ይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከም​ድር ላይ ውኃው እንደ ጐደለ ዐወቀ። ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም። በኖኅ ዕድሜ በስ​ድ​ስት መቶ አንድ ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ውኃው ከም​ድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅም የሠ​ራ​ትን የመ​ር​ከ​ቢ​ቱን ክዳን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ውኃው ከም​ድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ምድር ደረ​ቀች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፤ “አንተ ሚስ​ት​ህ​ንና ልጆ​ች​ህን፥ የል​ጆ​ች​ህ​ንም ሚስ​ቶች ይዘህ ከመ​ር​ከብ ውጣ። ከአ​ንተ ጋር ያሉ​ትን አራ​ዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር አው​ጣ​ቸው፤ በም​ድ​ርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት።” ኖኅም ሚስ​ቱን፥ ልጆ​ቹ​ንና የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ይዞ ወጣ፤ አራ​ዊት ሁሉ፥ እን​ስ​ሳም ሁሉ፥ ወፎ​ችም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከመ​ር​ከብ ወጡ። ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም። በም​ድር ዘመን ሁሉ መዝ​ራ​ትና ማጨድ፥ ብር​ድና ሙቀት፥ በጋና ክረ​ምት፥ ቀንና ሌሊት አያ​ቋ​ር​ጡም።”

ዘፍጥረት 8:1-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከርሱ ጋራ የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ። የጥልቁ ምንጮችና የሰማይ ውሃ መስኮቶች ተዘጉ፤ ዝናቡም መዝነቡን አቆመ። ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ ዐምሳ ቀን በኋላም ጐደለ። በሰባተኛው ወር፣ በዐሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ ዐረፈች። ውሃው እስከ ዐሥረኛው ወር ድረስ እየቀነሰ መጣ፤ በዐሥረኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ጫፎች ታዩ። ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቧን መስኮት ከፍቶ፣ ቍራን ወደ ውጭ ላከ፤ ቍራውም ውሃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። ከዚያም በኋላ፣ ኖኅ ውሃው ከምድር ገጽ ጐድሎ እንደ ሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤ ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት። ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደ ገና ላካት። እርሷም ወደ ማታ ተመለሰች፤ እነሆም የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ነበር፤ ያን ጊዜ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጕደሉን ዐወቀ። ሰባት ቀንም ቈይቶ ርግቧን እንደ ገና ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቧ ወደ እርሱ አልተመለሰችም። ኖኅ በተወለደ በስድስት መቶ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። ኖኅ በመርከቡ ላይ ያለውን ክዳን አንሥቶ ተመለከተ፤ የመሬቱም ገጽ እንደ ደረቀ አየ። በሁለተኛው ወር፣ በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች። ከዚያም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቧ ውጡ። እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ፣ ከአንተ ጋራ ያሉትን ወፎች፣ እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።” ኖኅም ከልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋራ ወጣ። እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ። ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም። “ምድር እስካለች ድረስ፣ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት፣ አይቋረጡም።”

ዘፍጥረት 8:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ኖኅን፤ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዋቱን ሁሉ፤ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ነፉስን አሳለፈ፤ ውኂውም ጎደለ የቀላዪም ምንጮች የሰማይም መስኮቶች ተደፈኑ፤ ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ ውኂውም ከምድር ላይ እያደር እያደር ቀለለ፤ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኂው ጎደለ። መርከቢቱም በስባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች፤ ላይ ተቀመጠች። ውኂውም እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበረ፤ በአሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበር በአሥረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮች ራሶች ተገለጡ። ከአርባ ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ፤ ቁራንም ሰደደው እርሱም ወጣ፤ ውኂው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት። ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አለገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች ውኃ በምድር ላይ ሁሉ ስለ ነበረ እጁን ዘረጋና ተቀበላት ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት። ከዚያም በኋላ ደግሞ እስከ ስባት ቀን ቆየ ርግንም እንደ ገና ከመርከብ ሰደደ። ርግብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች በአፍዋም እነሆ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃ እንደ ቀለለ አወቀ። ደግሞ እስከ ሰባት ቀም ቆየ ርግብንም ሰደዳት ዳግመኛም ወደ እርሱ አልስተመለሰችም። በኖኅ ዕድሜ በስድስት መቶ አንድ ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ክዳን አነሣ፥ እነሆም ውኃው ከምድር ፊት እንደ ደረቀ አየ። በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛውም ወር ቀን ምድር ደረቀች። እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ አንተ ሚስትህንና ልጆችህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመርከብ ውጣ። ከአንተ ጋር ያሉትን አራዊት ሁሉ ሥጋ ያላቸውን ሁሉ፥ ወፎችንና እንስሶችን ሁሉ፥ ከአንተ ጋር አውጣቸው በምድር ላይ ይብዙ። ኖኅም ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወጣ። አራዊት ሁሉ፥ ተቀሳቃሾች ሁሉ፥ ወፎችም ሁሉ በምድር ላይ የሚርመሰምስው ሁሉ በየዘመዳቸው ከመርከብ ወጡ። ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጽሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችን ሁሉ ወሰደ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀርበ። እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ ምድርን ዳግመኛ ስለ ስው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉት እንደ ገና አልመታም። በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።

ዘፍጥረት 8:1-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ፤ ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም መጒደል ጀመረ። ከምድር በታች ያሉት ጥልቅ ምንጮች፥ በሰማይ ያሉት የውሃ መውረጃ በሮች ሁሉ ተዘጉ፤ ዝናቡም ከሰማይ መውረዱን አቆመ። ውሃው ቀስ በቀስ ከምድር ላይ መጒደል ጀመረ፤ ከመቶ ኀምሳ ቀኖችም በኋላ ውሃው ከምድር ላይ በጣም ጐደለ። በሰባተኛው ወር፥ በዐሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቡ “አራራት” ከተባሉት ተራራዎች በአንደኛው ጫፍ ላይ ዐረፈ። ውሃው እስከ ዐሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየጐደለ ሄደ፤ በዐሥረኛው ወር መጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ጫፎች ታዩ። ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቡን መስኮት ከፈተ፤ ቊራን ወደ ውጪ ላከው፤ ቊራውም ውሃው ከምድር እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። ከዚህ በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጒደሉን ለማወቅ አንዲት ርግብ ላከ። ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት። ሰባት ቀን ከቈየም በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት። እርስዋም ወደ ማታ ጊዜ የለመለመ የወይራ ዘይት ዛፍ ቅጠል በአፍዋ ይዛ ወደ ኖኅ ተመለሰች፤ በዚህ ሁኔታ ኖኅ ውሃው ከምድር መጒደሉን ዐወቀ። ደግሞም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ኖኅ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ በዚህን ጊዜ ግን ርግቢቱ ሳትመለስለት ቀረች። የኖኅ ዕድሜ 601 ዓመት በሆነ ጊዜ በመጀመሪያው ወር፥ በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፤ ምድሪቱ እንደ ደረቀች አየ። በሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድር ፈጽማ ደረቀች። እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “አንተ ከሚስትህ፥ ከልጆችህና ከልጆችህ ሚስቶች ጋር ሆነህ ከመርከቡ ውጣ፤ ተራብተውና ተባዝተው ምድርን ሁሉ እንዲሞሉ ከአንተ ጋር ያሉትን ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ወፎችን፥ እንስሶችንና ሌሎችን በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረቶች ሁሉ ይዘህ ውጣ።” ከዚህ በኋላ ኖኅ ከሚስቱ፥ ከልጆቹና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ሆኖ ከመርከቡ ወጣ፤ አራዊትና እንስሶች፥ ወፎችም በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችም በየወገናቸው ሆነው ከመርከቡ ወጡ። ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዐይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው። የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም። ምድር እስካለች ድረስ፥ ለመዝራትና ለማጨድ፥ ለብርድና ለሙቀት፥ ለበጋና ለክረምት፥ ለቀንና ለሌሊት የማያቋርጥ ጊዜ ይኖራል።”

ዘፍጥረት 8:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥ ከምድር በታች ያሉት ታላቅ የውሃ መፍለቂያዎች፥ በሰማይ ያሉት የውሃ መውረጃ በሮች ሁሉ ተዘጉ፤ ዝናቡም ከሰማይ መውረዱን አቆመ። ውሃው ቀስ በቀስ ከምድር ላይ ቀለለ፥ ከመቶ አምሳ ቀንም በኋላ ውኃው ጎደለ። መርከቢቱም በሰባተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች በአንደኛው ጫፍ ላይ ዐረፈች። ውኃውም እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበረ፤ በአሥረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ጫፎች ተገለጡ። ከአርባ ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ፥ ቁራንም ወደ ውጪ ላከው፤ እርሱም ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። ከዚህ በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጉደሉን ለማወቅ አንዲት ርግብ ላከ። ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት። ሰባት ቀን ከቈየም በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት። ርግብም ወደ ማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሰች፥ እነሆም፥ በአፍዋ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከምድር ላይ ውኃው መጉደሉን አወቀ። ደግሞም ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ ዳግመኛም ወደ እርሱ ሳትመለስለት ቀረች። የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ አንድ በሆነ ጊዜ፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ውኃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፤ ምድሪቱ እንደ ደረቀች አየ። በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛው ቀን ምድር ፈጽማ ደረቀች። እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ አለው፦ “አንተ ከሚስትህ፥ ከልጆችህና ከልጆችህ ሚስቶች ጋር ሆነህ ከመርከቡ ውጣ፤ ተራብተውና ተባዝተው ምድርን ሁሉ እንዲሞሉ ከአንተ ጋር ያሉትን ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ወፎችን፥ እንስሶችንና ሌሎችን በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረቶች ሁሉ ይዘህ ውጣ።” ከዚህ በኋላ ኖኅ ከሚስቱ፥ ከልጆቹና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ሆኖ ከመርከቡ ወጣ፤ አራዊትና እንስሶች፥ ወፎችም በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችም በየወገናቸው ሆነው ከመርከቡ ወጡ። ኖኅም ለጌታ መሠውያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዓይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው። የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም። በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም።”