ኢሳይያስ 40:30-31
ኢሳይያስ 40:30-31 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ብላቴኖች ይራባሉ፤ ጐልማሶች ይታክታሉ፤ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይዝላሉ። እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡኢሳይያስ 40:30-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፤ ይታክታሉም፤ ጐበዛዝትም ተሰናክለው ይወድቃሉ። እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡኢሳይያስ 40:30-31 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፥ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡኢሳይያስ 40:30-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፥ ይታክታሉም፤ ጐልማሶችም ዝለው ይወድቃሉ፤ በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን ኀይላቸው ይታደስላቸዋል። እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።
Share
ኢሳይያስ 40 ያንብቡ