ኢሳይያስ 52:7
ኢሳይያስ 52:7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሰላምን የሚያወራ፥ መልካም የምሥራችንም የሚናገር፥ መድኀኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፥ “አምላክሽ ነግሦአል” የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
ኢሳይያስ 52:7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል!” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።
ኢሳይያስ 52:7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።