ኢሳይያስ 56:2
ኢሳይያስ 56:2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ይህን የሚያደርግ በእርሱም ጸንቶ የሚኖር፥ ሰንበታትንም የሚጠብቅና የማያረክስ፥ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”
ኢሳይያስ 56:2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣ እነዚህን የሚፈጽም ሰው ብፁዕ ነው።”
ኢሳይያስ 56:2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።