ኢሳይያስ 60:16
ኢሳይያስ 60:16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፤ የነገሥታትንም ብልጽግና ትበያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ፥ መድኀኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
ኢሳይያስ 60:16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
ኢሳይያስ 60:16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የአሕዛብንም ወተት ትጠጫልሽ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፥ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃያል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።