ኤርምያስ 14:20-21
ኤርምያስ 14:20-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ በአንተ ላይ ኀጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን። ስለ ስምህ ብለህ ተመለስልን፤ የክብርህንም ዙፋን አታጥፋ፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።
ኤርምያስ 14:20-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፋታችንን ዐውቀናልና፤ የአባቶቻችንን በደል ተረድተናልና፤ በርግጥም በአንተ ላይ ኀጢአት ሠርተናል። ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፤ የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ። ከእኛ ጋራ የገባኸውን ኪዳን ዐስብ፤ አታፍርሰውም።
ኤርምያስ 14:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አቤቱ፥ በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን። ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፥ የክብርህንም ዙፋን አታስነውር፥ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።