ኤርምያስ 38:9-10
ኤርምያስ 38:9-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው በእርሱ ላይ በአደረጉት ሁሉ ክፉ አድርገዋል፤ በከተማዪቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።” ንጉሡም ኢትዮጵያዊዉን አቤሜሌክን፥ “ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፤ ነቢዩ ኤርምያስም ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው።
ኤርምያስ 38:9-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ በኤርምያስ ላይ ባደረጉት ነገር ሁሉ ክፋትን አድርገዋል፤ ከከተማዪቱም እንጀራ በጠፋ ጊዜ በራብ እንዲሞት ጕድጓድ ውስጥ ጥለውታል።” ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቢሜሌክን፣ “ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው።
ኤርምያስ 38:9-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው በእርሱ ላይ በማድረጋቸው ሁሉ ክፉ አድርገዋል፥ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ ይሞታል። ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፦ ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው።