ኢዮብ 4:4-6 - ሁሉንም ስሪቶች ያወዳድሩ

ኢዮብ 4:4-6 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም። ንጽሕናህ መታመኛህ፣ ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?

ኢዮብ 4:4-6 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ቃሎችህ የሚሰናከሉትን ይደግፉ ነበር፤ የሚብረከረኩትንም ጒልበቶች ታበረታ ነበር። አሁን ግን ችግር ስለ መጣብህ ተስፋ ቢስ ሆነሃል፤ ችግሩም ስለ በረታብህ ተስፋ ቈርጠሃል። አምላክህን መፍራትህ መተማመኛህ፥ ትክክለኛ መንገዶችህም፥ ተስፋህ አይደለምን?

ኢዮብ 4:4-6 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በቃ​ልህ በሽ​ተ​ኞ​ችን ታስ​ነሣ ነበር፥ የሚ​ብ​ረ​ከ​ረ​ከ​ው​ንም ጕል​በት ታጸና ነበር። አሁን ግን ሕማም በአ​ንተ ላይ መጥቶ ዳሰ​ሰህ። አን​ተም ተቸ​ገ​ርህ። ጥን​ቱን ፍር​ሀ​ትህ፥ ተስ​ፋ​ህም፥ የመ​ን​ገ​ድ​ህም ጠማ​ማ​ነት፥ ስን​ፍና አይ​ደ​ለ​ምን?

ኢዮብ 4:4-6 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተቸገርህ። አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?

ኢዮብ 4:4-6 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጉልበት ታጸና ነበር። አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቷል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተረበሽህ። አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?