ሉቃስ 4:5-8
ሉቃስ 4:5-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዲያብሎስም ወደ ረዥም ተራራ አወጣው፤ የዓለምን መንግሥታትም ሁሉ በቅፅበት አሳየው። ዲያብሎስም እንዲህ አለው፥ “ይህን ሁሉ ግዛት፥ ይህንም ክብር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ለእኔ ተሰጥቶአልና፤ ለወደድሁትም እሰጠዋለሁና። ስለዚህ አንተ በፊቴ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ ለአንተ ይሁንልህ።” ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ሰይጣን ከኋላዬ ሂድ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ልትሰግድ፥ እርሱንም ብቻ ልታመልክ ተጽፎአል” አለው።
ሉቃስ 4:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍታ ቦታ አውጥቶት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው፤ እንዲህም አለው፤ “የእነዚህ መንግሥታት ሥልጣንና ክብር ሁሉ ለእኔ ተሰጥቷል፤ እኔም ለምወድደው ስለምሰጥ፣ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ስለዚህ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።
ሉቃስ 4:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው። ዲያብሎስም፦ ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።
ሉቃስ 4:5-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህም በኋላ ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ አንድ ከፍተኛ ቦታ ላይ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው። “ይህን ሁሉ ሥልጣንና ክብር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ይህ ሁሉ ለእኔ የተሰጠኝ ስለ ሆነ ለፈለግሁት መስጠት እችላለሁ፤ ስለዚህ አንተ ለእኔ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል፤” አለው። ኢየሱስም፦ “ለጌታ ለአምላክህ ብቻ ስገድ! እርሱንም ብቻ አምልክ! ተብሎ ተጽፎአል፤” ሲል መለሰለት።