ነህምያ 6:15-16
ነህምያ 6:15-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ቅጥሩም በኤሉል ወር በሃያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ። እንዲህም ሆነ፤ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ አይተውም እጅግ ተደናገጡ፤ ይህም ሥራ በአምላካችን እንደ ተፈጸመ አወቁ።
ያጋሩ
ነህምያ 6 ያንብቡነህምያ 6:15-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቅጥሩም ኤሉል በተባለው ወር ሃያ ዐምስተኛ ቀን፣ በዐምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጠናቀቀ። ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን ሲሰሙ፣ በዙሪያችን ያሉ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ በራሳቸው መተማመንም አልቻሉም፤ ምክንያቱም ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን ርዳታ መሆኑን ተገንዝበዋል።
ያጋሩ
ነህምያ 6 ያንብቡነህምያ 6:15-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ። ጠላቶቻችንም ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ በራሳቸውም አሳብ እጅግ ተዋረዱ፥ ይህም ሥራ በእግዚአብሔር እንደ ተደረገ አወቁ።
ያጋሩ
ነህምያ 6 ያንብቡ