በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።
ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፥ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ። አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ ያለውንም ምሳሌ እናገራለሁ።
እርሱ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ አሁንም ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ። በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
Home
Bible
Plans
Videos