ሮሜ 1:26-28
ሮሜ 1:26-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ስለዚህም እግዚአብሔር ክፉ መቅሠፍትን አመጣባቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ትተው ለባሕርያቸው የማይገባውን ሠሩ። ወንዶችም እንዲሁ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን ትተው በፍትወት ተቃጠሉ፤ እርስ በርሳቸውም እየተመላለሱ፥ ወንዶች በወንዶች ላይ የሚያዋርዳቸውን ነውር ሠሩ፤ ነገር ግን ፍዳቸውን ያገናሉ፤ ፍዳቸውም በራሳቸው ይመለሳል። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።
ሮሜ 1:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤
ሮሜ 1:26-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሰዎች ይህን በማድረጋቸው ምክንያት እግዚአብሔር ለማይገባ አስነዋሪ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸው እንኳ የተለመደውን ተፈጥሮአዊ ግንኙነት ባልተለመደ ግንኙነት ለወጡት። እንዲሁም ወንዶቹ የተለመደውን ግንኙነት ከሴቶች ጋር ማድረግ ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ስለዚህ ወንዶች ከወንዶች ጋር አሳፋሪ ነገር ፈጸሙ፤ በስሕተታቸውም ምክንያት የሚገባቸውን ቅጣት በሥጋቸው ይቀበላሉ። ሰዎች እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ አስነዋሪ ነገር እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።
ሮሜ 1:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ለሚያዋርድ ፍትወት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ተፈጥሮአዊውን ግንኙነት ተፈጥሮአዊ ባልሆነ ግንኙነት ለወጡ፤ እንዲሁም ደግሞ ወንዶች ተፈጥሮአዊ የሆነውን ከሴት ጋር መገናኘት ትተው እርስ በእርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም ከወንዶች ጋር ነውር ፈጸሙ፤ በስሕተታቸውም ምክንያት የሚገባቸውን ቅጣት በራሳቸው ላይ ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤