እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶችናሙና
![እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶች](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans-staging%2F50492%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
እውነታ
ሁሉም ወንጌላት በተለይም ማቴዎስ እንደተረከው የጴጥሮስን ታላቅ የውድቀት ታሪክ ከጀግንነቱና ከትክክልኛነቱ ጋር ዘግበውታል፡፡
በዚህ ክፍል የጰጥሮስ ውድቀትን የምንረዳው ሆኖ አገኘዋለሁ፤ ምክንያቱም ጴጥሮስ ባልቆመበት እኔ እቆም ነበር ለማለት አልችልምና፡፡
ከወንጌሉ እንደምንረዳው ከሰዓታት ቀደም ብሎ ጴጥሮስ በጌቴሴማኔ የአትክልት ስፍራ የሊቀ-ከህኑን አገልጋይ ጆሮ በመቁረጥ ኢየሱስን እንዳይያዝ ሲጥር እናያለን፡፡ ኋላ ግን ጴጥሮስ በዚህ ክፍል በሊቀ-ከህኑ ግቢ ውስጥ በአንዲት ገረድ ፊት በፍርሃት ሲርድ እናያለን፡፡
ከጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ ጴጥሮስ በብዙ ጀግንነትና በጥሩ መንፈስ ነበር፤ አሁን ግን በብዙ ሀፍረት፣ መራርነት፣ ተስፋ መቁረጥ እና እንባ ውስጥ ነው፡፡ ለኢየሱስ እሞትልሃለሁ ብሎ የማለው ጴጥሮስ አሁን ግን ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ጮክ ብሎ እየማለ እንደማያውቀው ሆነ። በአጭሩ ጴጥሮስ ወደቀ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደቀ፡፡
ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጴጥሮስ የውድቀት ታሪክ ብቸኛው አይደለም፡፡ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው እሰከ መጨረሻው በሰው የውድቀት ታሪክ እውነታ የተሞላ ነው፡፡
ምንም እንኳን በፍፁም ዓለም ውሰጥ በኖሩም አዳምና ሄዋን ወድቀዋል፡፡ አብርሃም ወድቋል፤ ስለሚስቱ ዋሽቷል፡፡ እስራኤላወያንን ከግብጽ የታደገው ሰው ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሳይገባ ቀረ፤ ወደቀ፡፡
እንደ ልቤ የተባለለት ዳዊት በሚያስደነግጥ ሁኔታ ወድቋል፤ ከቤርሳቤህ ጋር አመንዝሯል ባሏንም አስገድሏል፡፡ የዳዊት ልጅ ሰለሞን ዳግም ወደ እስራኤል ጣኦት አምልኮን እንዲያንሰራራ በማድረግ ወድቋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ሁሉ የእግዚአብሔር ህዝቦች ከአንዱ ትውልድ እስከ ሌላኛው ትውልድ ጣኦትን በጽኑ በማምለካቸውና ለእግዚአብሔር ደግሞ ባለመታዘዛቸው እንደወደቁ እናያለን፡፡
አዲስ ኪዳንም ስለ እግዚአብሔር ህዝብ ውድቀት በእኩል ደረጃ ይዘግባል፡፡ በእዚው በጴጥሮስ የክህደት ታሪክ ውስጥ እንኳን ማቴዎስ ሁሉም ደቀ-መዛሙርት በፍፁም እንደማይክድቱ ሲምሉ እንደነበር ነግሮን ኋላ ግን በወሳኙ ሰዓት ሁሉም ደቀ-መዛሙርት ክርስቶስን ትተዉት ሸሹ፡፡ ሁሉም ወደቁ፡፡
እኔ እንደማምነው የጴጥሮስ የውድቀት ታሪክ በሁሉም አራቱ ወንጌላት ውስጥ መፃፉ እኛ እንደ ክርስቲያን በእውነተኝነት ስለውድቀታችን እውነታና መኖር መቀበል እንዳለብን እየነገረን ነው፡፡ ዋነኛው የክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት መሪ ጴጥሮስ ወደቀ፡፡ እኔም አንተም ወድቀናል፡፡ በአንድም ይሁን በሌላ እኛ ሁላችን ወድቀናል፤ በመሆኑም እኛም ነን ጌታን የካድነው፡፡
ስናጠቃልለው ውድቀት በክርስትና ህይወታችን ልንቀበለው የተገባ እውነታና መጽሐፍ ቅዱስ በሚቀበለው እውነት ልክ በእውነተኛነት ልንቀበለውና ልንጋፈጠው ይገባል፡፡
ስለዚህ እቅድ
![እንደ ክርስቲያን የእኛ ውድቀቶች](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans-staging%2F50492%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
ይህ የሚያበረታታ የአምስት ቀን የንባብ ዕቅድ የሚዳስሰው እውነት በሉዓላዊነቱ እግዚአብሔር የእኛን ውድቀት አስቀድሞ ያያል እንዲሁም በርህራሄው ደግሞ ውድቀቶቻችንን ይቅር ይላል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Returning to the Gospel - East Africa ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://returningtothegospel.com/