ዮሐንስ 18:25-27

ዮሐንስ 18:25-27 NASV

ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ሲሞቅ፣ “አንተ ከርሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፣ “እኔ አይደለሁም” ሲል ካደ። ከሊቀ ካህናቱ ባሮች አንዱ ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ፣ “በአትክልቱ ስፍራ አንተን ከርሱ ጋራ አላየሁህም?” ሲል ጠየቀው። ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።