የዮሐንስ ወንጌል 18:25-27

የዮሐንስ ወንጌል 18:25-27 አማ54

ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። እንግዲህ፦ “አንተ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፦ “አይደለሁም” ብሎ ካደ። ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ ባሮች አንዱ፦ “በአትክልቱ ከእርሱ ጋር እኔ አይቼህ አልነበረምን?” አለው። ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፥ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።