ረሃብናሙና

ረሃብ

ቀን {{ቀን}} ከ4

ረሃብ የዕምነታችን ምልክት

እርግጠኛነኝአብራችሁጊዜለማሳለፍሁልጊዜየምትጠብቃቸውንሰዎችስምልትጠሩትችላላችሁ፡፡ይህንን በህይወታችን ብቻችንን እንድንፈፅም ብቻ አይደለም ያሰበው፡፡ እኛ በህብረት የተጋመድን ነን፤ ምክንያቱም ግንኙነትን ከሚፈልገው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርን ስለሆንን፡፡ እግዚአብሔርእኛንለመፍጠሩዋነኛመነሻውህብረትነበር፡፡እኛምእርሱንእንድናውቀው፤እርሱንምእንድንመስል እንዲሁም ክብሩንለዓለምእንድንገልጥይፈልጋል፡፡በእርግጥየሰውዘርበኃጥያትመውደቅእግዚአብሔርካሰበልንደስታጋርሊኖረንየነበረውንትክክለኛህብረትአጥፍቶታል፤ነገርግንበዚህፈንታእግዚአብሔርያቀደውነበር እርሱምኢየሱስ ነው፡፡

ምናልባት ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ለመውሰድ ባላቸው መሻት ምክንያት ህይወታቸው ፍፁም ስለመለወጡ የምትናገርላቸው ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባላት ይኖሩ ይሆናል፡፡ አንተም ይህንን መሰል ሕይወት ተለማምደህም ይሆናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ ማለት እግዚአብሔርን በብዙ ለሚራብ ሰው እጅግ አስፈላጊ ምላሽ ነው፡፡ በሌላ አባባል ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ህብረት ያለን ረሃብ ማለትም በፀሎት፣ በአምልኮና በቃሉ ጊዜ ማሳለፉ የእምነታችን የልብ ትርታ ነው፡፡ ዳዊት በዚህ ረገድ ሲገልፅ፤ “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ በህይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፤ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን አይ ዘንድ፤ በመቅደሱም እርሱን እፈልገው ዘንድ” (መዝሙር 27፤4)

ሁሉም ሰው የምግብ ተፈጥሮአዊ ረሃብ አለው፤ ምክንያቱም ምግብ በህይወት ለመቆየትና ለሰውነት ጤንነት የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮችን በመያዙ ነው። በመንፈሳዊውም እኛ በተፈጥሮ በውስጣችን እግዚአብሔርን መራብ አለን፤የምንረካውም በፊቱ የጥሞናና ሰፊ ጊዜን በጸሎት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጥናት ስናሳልፍ ነው። ዳዊት ሙሉ ህይወቱን የኖረው ለእግዚአብሔር ነው። የእርሱም ዋነኛ ፍላጎት ነው፤ ይህም ነውእግዚአብሔር እንደ ልቤ ብሎ እንዲገልጸው ምክንያት የሆነው። በዳዊት ህይወት ውስጥ ያየነውን አይነት ለእግዚአብሔር መቅናት ቢኖረን የምናመጣውን ተጽእኖ አስቡት።የእግዚአብሔርን የፍቅር እሳት እያበራን ብንቆይ፣ ችግሮችን እየጠረግንና ጨክነን ክርስቶስ ላይ ካተኮርን በኛ ዙሪያ ያለውን ዓለም እንዴት እንደምንቀይር አስቡት።

ሉቃስ 10 ላይ ስለ ሁለት እህትማማቾች ታሪክ ይነግረናል፤ ማርያምና ማርታ በቤታቸው እየሱስን ሲያስተናግዱ። ማርያም በኢየሱስ እግር ስር ስትቀመጥ ማርታ ግን የእርሱን ውጫዊ ፍላጎት ለማሟላት ትባክን ነበር። ኢየሱስም አላት “ማርታ ማርታ ስለምን ትጨነቂያለሽ በብዙም ትናደጃለሽ ነገር ግን የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው። ማሪያም የተሻለውን መርጣለች ከእርሷም አይወሰድባትም።ኢየሱስ ማርታን ወደ ራሱ መገኘት እየጋበዛት እንጂ ማርታን እየወቀሳት አይደለም። አንተንም እየጋበዘህ ነው። እግዚአብሔር እርሱን በቅርበት የማወቅ ረሃብ እያደገብህ የሚሄድ ሰው ትሆን ዘንድ ማስተዋል ይስጥህ። እግዚአብሔር በመገኘቱ ውስጥ ጊዜ ትወስድ ዘንድ፣ ይለውጥህ ዘንድ፣ እየጨመረ እየጨመረ እርሱን ወደ መምሰል ያበቃህ ዘንድ ያነቃቃህ፤ ከዚህም የተነሳ ሌሎች እርሱን መራብ ይጀምሩ፡፡

ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ረሃብ

ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ በህይወታችን እግዚአብሔርን ለማወቅና እርሱ እንዲታወቅ ማድረጋችን እኛን ወደ እርሱ ዓላማ እንዴት እንደሚገፋን ይዳስሳል፡፡ ዳዊትን እግዚአብሔር እንደ ልቤ እንዲለው ያደረገው ምን እንደሆነ እወቅና አንተስ እንዴት በሙሉ ትኩረትህ በእግዚአብሔር ፍቅር መኖር እንደምትችል እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ባለህ ህብረት በመደሰትና ፍላጎቶችህን እንደሚፈፅም ስለማመንም ጭምር፡፡ ይህ ዕቅድ የበለፀገው በዩቨርዥን ነበር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Lawrence Oyor ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.youtube.com/lawrenceoyor