1
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:25-26
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ። ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
Compare
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:25-26
2
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:23-24
ከጌታ የተቀበልኩትና ለእናንተም ያስተላለፍኩላችሁ ትምህርት ይህ ነው፤ ጌታ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት ኅብስት አነሣ፤ የምስጋናም ጸሎት አድርጎ ቈረሰውና “[እንካችሁ ብሉ፤] ይህ ለእናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:23-24
3
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:28-29
ስለዚህ ማንም ሰው ይህን ኅብስት ከመብላቱና ይህንንም ጽዋ ከመጠጣቱ በፊት ራሱን መመርመር አለበት። ማንም ሰው የጌታ ሥጋ ምን መሆኑን ለይቶ ሳያውቅ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታን ጽዋ ቢጠጣ በራሱ ላይ ፍርድን ያመጣል።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:28-29
4
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27
ማንም ሰው ያልተገባው ሆኖ ሳለ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታንም ጽዋ ቢጠጣ የጌታን ሥጋና ደም በማቃለሉ ይጠየቅበታል።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27
5
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ።
Explore 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1
Home
Bible
Plans
Videos