1
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:45
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተገዳደርኸው የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ ሁሉን በሚችል በሠራዊት ጌታ ስም እመጣብሃለሁ።
Compare
Explore 1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:45
2
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:47
እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ ጌታ ያለ ሰይፍ ወይም ያለ ጦር እንደሚያድን ያውቃሉ፤ ሰልፉ የጌታ ስለ ሆነም ሁላችሁን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።”
Explore 1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:47
3
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:37
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ ጌታ አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሲል ዳዊት ተናገረ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ ጌታ ካንተ ጋር ይሁን!” አለው።
Explore 1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:37
4
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:46
ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።
Explore 1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:46
5
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:40
ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ፤ አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች ከወንዝ መርጦ በእረኛ ኮረጆው ከጨመረ በኋላ፥ ወንጭፉን በእጁ ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ።
Explore 1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:40
6
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:32
ዳዊትም ሳኦልን፥ “ከዚህ ፍልስጥኤማዊ የተነሣ የማንም ሰው ልብ አይሸበር፤ እኔ አገልጋይህ ሄጄ እዋጋዋለሁ” አለው።
Explore 1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:32
Home
Bible
Plans
Videos