1
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:19
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:19
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:2
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:2
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:18
የፊተኛውን ነገር አታስታውሱ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:18
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:1
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:1
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:4
በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ፥ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:4
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:3
እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ ጌታ መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ እሰጣለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:3
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:5
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:5
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:25
መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም አላስብም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:25
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:10
ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም አገልጋዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል ጌታ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይኖርም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:10
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:11
እኔ፥ እኔ ጌታ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:11
11
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:13
እኔም አምላክ ነኝ፥ ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው?
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:13
12
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:20-21
የምድረ በዳ አራዊት፤ ቀበሮዎችና ሰጎኖች ያከብሩኛል፤ ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ ላጠጣ፥ በምድረ በዳ ውሃ፤ በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁ። ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብ ምስጋናዬን እንዲያውጅ ይህን አደርጋለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:20-21
13
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:6-7
ሰሜንን፦ “መልሰህ አምጣ፥” ደቡብንም፦ “ልቀቅ፥ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ አምጣ እለዋለሁ፤ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:6-7
14
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:16-17
ጌታ እንዲህ ይላል፥ በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤ ሠረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል፥ እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም፤ ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:16-17
15
ትንቢተ ኢሳይያስ 43:15
ቅዱሳችሁ፥ የእስራኤል ፈጣሪ፥ ንጉሣችሁ፥ ጌታ እኔ ነኝ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 43:15
Home
Bible
Plans
Videos