1
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:17
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አሁንም በክርስቶስ የሆነው ሁሉ አዲስ ፍጥረት ነው፤ የቀደመውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ።
Compare
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:17
2
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:21
ኀጢአት የሌለበት እርሱ እኛን ለእግዚአብሔር ያጸድቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድርጓልና።
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:21
3
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:7
በእምነት እንኖራለን፤ በማየትም አይደለም።
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:7
4
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:18-19
ነገር ግን ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ከአስታረቀን፥ የማስታረቅ መልእክትንም ከሰጠን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ኀጢአታቸውን ይቅር ብሎ በደላቸውንም ሳያስብ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቆአልና፤ የዕርቅ ቃሉንም በእኛ ላይ አደረገ፤ የይቅርታውንም መልእክት ሰጠን።
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:18-19
5
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:20
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:20
6
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:15-16
በሕይወት የሚኖሩትም ስለ እነርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞተውና ለተነሣውም እንጂ ወደፊት ለራሳቸው የሚኖሩ እንዳይሆኑ እርሱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ። ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:15-16
7
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:14
የክርስቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እንድንጸና ያስገድደናል፤ ሁሉ ፈጽመው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶአልና።
Explore ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 5:14
Home
Bible
Plans
Videos