1
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:45
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን አለው፦ አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፥ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
Compare
Explore አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:45
2
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:47
ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደል ያውቅ ዘንድ ነው። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፥ እናንተንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:47
3
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:37
ዳዊትም፦ ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል አለው።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:37
4
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:46
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፥ እመታህማለሁ፥ ራስህንም ከአንተ አነሣዋለሁ፥ የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ታውቅ ዘንድ፥
Explore አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:46
5
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:40
በትሩንም በእጁ ወሰደ፥ ከወንዝም አምስት ድብልብል ድንጋዮችን መረጠ፥ በእረኛ ኮረጆውም በኪሱ ከተታቸው፥ ወንጭፍም በእጁ ነበረ፥ ወደ ፍልስጥኤማዊውም ቀረበ።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:40
6
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:32
ዳዊትም ሳኦልን፦ ስለ እርሱ የማንም ልብ አይውደቅ፥ እኔ ባሪያህ ሄጄ ያንን ፍልስጥኤማዊ እወጋዋለሁ አለው።
Explore አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:32
Home
Bible
Plans
Videos