YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 120

120
ከሐሰተኞችና ከአታላዮች ለመዳን የሚቀርብ ጸሎት
1መከራ በደረሰብኝ ጊዜ፥
ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ፤
እርሱም ሰማኝ።
2እግዚአብሔር ሆይ!
ከሐሰተኞችና ከአታላዮች አድነኝ።
3እናንተ አታላዮች!
እግዚአብሔር እናንተን ምን ቢያደርጋችሁ ይሻላል?
እንዴትስ ቢቀጣችሁ ይሻላል?
4በተሳለ የወታደር ፍላጻ ይወጋችኋል፤
በከሰል ፍምም ያቃጥላችኋል።
5በቄዳር ሕዝብ መካከል
በሜሼክ ስደተኛ ሆኜ በመኖሬ ወዮልኝ!
6ሰላምን ከሚጠሉ ሕዝቦች ጋር
እጅግ ለረጅም ጊዜ ኖርኩ።
7እኔ ሰላምን እደግፋለሁ፤
ስለ ሰላም በምናገርበት ጊዜ እነርሱ ስለ ጦርነት ያወራሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in